የአሜሪካ ህጋዊ ቋሚ ነዋሪዎች (LPR)

ይህ ድህረ ገጽ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የመግቢያ ሰነድ ለሌላቸው ተመላሽ ለሆኑ ሕጋዊ ቋሚ ነዋሪዎች መጠነኛ ድጋፍ ይሰጣል።

የሚከተሉትን የቆንስላ አገልገሎቶች ለመጠቀም አካውንት ይክፈቱ

  • ተመላሽ አሜርካዎ ቋሚ የመኖሪያ ካርዱን ያጣ ነገር ግን ከአንድ አመት በታች ከአሜርካ ሀገር ውጪ የቆየ LPR የቦርዲንግ ፎይል ቃለመጠይቅ እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይችላል፡፡
  • ተመላሽ አሜርካዊ ከአንድ አመት በላይ ከአሜርካ ውጪ የቆየ LPR የመመለሻ ቪዛ ቃለመጠይቅ ቀጠሮ እንዲደረግለት ሊያደርግ ይችላል፡፡

ማሳሰቢያ: ከላይ የተጠቀሱት እርስዎን የማይመለከቱ ከሆነ ወደ ጥሪ ማዕከሉ አይደውሉ።

ለአሜሪካ ህጋዊ ቋሚ ነዋሪዎች (LPRs) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ USCISCBP፣ ወይም https://travel.state.gov ይጎብኙ፡፡

ለቦርዲንግ ፎይል ማመልከቻዎች ሊሟሉ የሚገቡ ሰነዶች፡

  • የታደሰ ፓስፖርት
  • የፖሊስ ሪፖረት (ግሪን ካርድዎ ጠፍቶ ወይም ተሰርቆ የሆነ እንደሆነ)
  • I-131A ፎርም ከ https://www.uscis.gov/i-131a ለቃለመጠይቅ ሲመጡ ይህ ፎርም ተሞልቶ ተፈርሞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • አንድ መደቡ ነጭ የሆነ ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶግራፍ. ለበለጠ መረጃ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/visa-information-resources/photos.html ይጎብኙ
  • ተገቢውን ተመላሽ ያልሆነ የማመልከቻ ክፍያ በ USCIS ኦንላይን መክፍያ ሲስተም https://my.uscis.gov/travel-document/eligibility ከፍለው የክፍያውን ደረሰኝ አትመው ይዘው ይቅረቡ
  • መጨረሻ ከአሜሪካ የወጡበትን ግዜ የሚያሳይ ማስረጃ
    • ከፓስፖርትዎ ላይ የአሜሪካ መውጫና መግቢያ በ "A" የሚጀምር ቁጥር ያለው ማህተም
    • የአውሮፕላን ቲኬት፣ ቦርዲንግ ፓስ፣ የጉዞ ቀንና ሰዓት ዝርዘር መረጃ

ለተጨማሪ መረጃ ይህንን ድህረገፅ ይጎብኙ https://et.usembassy.gov/visas/immigrant-visas/returning-resident-visa/

ለተመላሽ ነዋሪ ቪዛ የሚያስፈልጉ ወረቀቶች

ለተጨማሪ መረጃ ይህንን ድህረገፅ ይጎብኙ https://et.usembassy.gov/visas/immigrant-visas/returning-resident-visa/