የዩኤስ ኢሚግራንት ቪዛ አመልካቾች እንኳን ደህና መጣችሁ

ለዩናይትድ ስቴትስ ቆንስላ ሚሲዮን ኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ የኢሚግራንት (ቋሚ) ቪዛ ድጋፍ የድርጣቢያ ላይ ነዎት።

ኖቭል ኮሮናቫይረስን በተመለከተ ለቪዛ አመልካቾች የወጣ አስቸኳይ መረጃ

ማንኛውም ለቪዛ ማመልከቻ የኮንስላር ቃለመጠይቅ ቀጠሮዎችን በመጠባበቅ ላይ ያለ ግለሰብ ማለትም (1) ባለፉት 14 ቀናት በቻይና ሕዝባዊ ሪፖብሊክ ሆንግ ኮንግ እና ማካው ልዩ አስተዳደራዊ ክልሎችን ሳይጨምር የነበረ፣ (2) የጉንፋን አይነት ምልክቶች እየተሰማው ያለ (3) ለኖቭል ኮሮናቫይረስ ተጋልጦ ሊሆን እንደሚችል የሚያምን ፣ ቀጠሮውን ቢያንስ በ14 ቀናት እንዲያስተላልፍ በጥብቅ ይበረታታል:: ቀጠሮውን ለመቀየር ምንም አይነት ተጨማሪ ክፍያ አይኖርም፡፡ የቪዛ ማመልከቻ ክፍያዎች በተከፈለበት ሀገር ውስጥ ለአንድ ዓመት ያህል ያገለግላሉ።

ቀጠሮዎን ወደ ሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ፣ እባክዎ ወደ የተጠቃሚ መለያዎ ይግቡ ፣ የቡድን እርምጃ ከሚለው ስር “ቀጠሮ ዳግም ያስይዙ” የሚለውን አማራጭ መርጠው ያለውን የስርዓት መመሪያዎች ይከተሉ። ተጨማሪ እርዳታ ከፈለጉ እባክዎን ከገጹ ታችኛው ክፍል የሚገኘውን “ያነጋግሩን” ሚለውን ክፍል ይመልከቱ ።

ተጨማሪ ሙሉውን ለማየት

የቆንስላ የስደተኛ ቪዛ ቀጠሮዎን ቀንና ሰዓት ያስመዝግቡ ወይንም ለተመላሽ ነዋሪ የድጋፍ አገልግሎቶችን ይጠይቁ፡፡

ያስያዙትን የቆንስላ የስደተኛ ቪዛ ቀጠሮዎን ወይንም የተመላሽ ነዋሪ ጥያቄዎን ደግመው ይመልከቱ ወይንም ያስተዳድሩ፡፡

ስለ ስደተኛ ቪዛ የማመልከቻ ሂደት ተጨማሪ ይወቁ፡፡