ስለ ስደተኛ ቪዛ የሚነሱ ጥቄዎችና መልሶቻቸው

አጠቃላይ መረጃ

  1. የዚህ ድህረ ገጽ አላማ ምንድን ነው?
  2. የይለፍ ቃሌን እረሳሁ. የይለፍ ቃሌን እንዴት ዳግም መቀየር እችላለሁ?
  3. ወደ መለያዬ ለመግባት ጥቅም ላይ የዋለውን ኢሜይል እንዴት መቀየር እችላለሁ?
  4. የአሜሪካ ቪዛ ሳመለክት የማህበራዊ ሚድያ መለያየን እንዳሳውቅ የሚያዝ መመሪያ አለ ወይ?

የስደተኛ ቪዛ መረጃ

  1. የስደተኛ ቪዛ ምንድን ነው?
  2. ለስደተኛ ቪዛ ለማመልከት የሚያስችል ማመልከቻ በእኔ ስም ገብቷል፤ ነገር ግን ማመልከቻው አሁንም በአሜሪካ የዜግነትና የስደተኛ አገልግሎቶች (USCIS) ይገኛል፤ ማመልከቻው ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ እንዴት ማጣራት እችላለሁ?
  3. ለስደተኛ ቪዛ ለማመልከት ምን ያህል ያስከፍላል?

የስደተኛ ቪዛ የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ

  1. ጉዳዬ በብሔራዊ የቪዛ ማዕከል (National Visa Center - NVC) ይገኛል፤ ይህንን ቢሮ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?
  2. ቀጠሮ እንደተያዘልኝ እንዴት አውቃለሁ?
  3. በቃለ መጠይቁ ወቅት ምን ይዤ መቅረብ ይኖርብኛል?
  4. ቃለ መጠይቅ አድርዴ በአንቀጽ 221(g) መሠረት ተጨማሪ ሰነድ ወይንም መረጃ ምክንያት ተከልክያለሁ፡፡ ይህን ለማቅረብ አሁን ዝግጁ ነኝ - ይህንን እንዴት ለማድረግ እችላለለሁ? ወደ ኤምባሲው በድጋሚ መምጣት ይኖርብኛል?
  5. የቃለ መጠይቅ ቀጠሮዬ ካመለጠኝ ወይንም ካለፈኝ ምን ማድረግ ይገባኛል?

የቪዛ ጥቅል ሰነዶች እና ዘመናዊው የኢሚግራንት (የነዋሪነት) ቪዛ

  1. ጥያቄ፡ በቅርቡ የኢሚግራንት ቪዛ ቃለመጠይቅ አድርጌ ቪዛዬን ተረክቤአለሁ፡፡ ነገርግን አብሬ ይዤው የሚሄደው የታሸገ ፖስታ አልተሰጠኝም፡፡ ጠበቃዩ/ የሚወስደኝ ግለሰሰብ ወይም ጎደኞቼ ያለዚህ ፖስታ መብረር እንደሌለብኝ ነግረውኛል፡፡ ምን ማድረግ ነው ያለብኝ ?
  2. ጥያቄ፡ የሲቪል ወይም የፋይናንስ ሰነዶቼን በ CEAC ድህረገጽ በኤሌክትሮኒክ መንገድ ወይም በሌላ መንገድ ልላክ አላስታውስም ፡፡ ቪዛዬ በወረቀት አልባው አሰራር እንደተሠጠኝ ማወቅ የምችልበት መንገድ አለ ወይ ?
  3. ጥያቄ፡ አንዳንድ ሰዎች በእጅ ተይዞ የሚገባ የታሸገ ፖስታ ሲሰጣቸው አውቃለሁ የኔ ከነሱ ለም ተለየ ?

ህጋዊ ቋሚ ነዋሪ (የቋሚ ነዋሪነት መታወቂያ -ግሪን ካርድ – የያዙ)

  1. በቅርቡ የሚቃጠል የቋሚ ነዋሪነት መታወቂያ (ግሪን ካርድ) አለኝ፣ አዲስ መታወቂያ/ካርድም አልደረሰኝም፡፡ ወደ አሜሪካ እንዴት ተመልሼ መግባት እችላለሁ? ህጋዊነቴን አጥቻለሁ?
  2. የቋሚ ነዋሪነት መታወቂያ (ግሪን ካርድ) አለኝ፣ ነገር ግን ከአሜሪካ ውጪ ከአንድ ዓመት በላይ ቆይቻለሁ፡፡ ወደ አሜሪካ ተመልሼ ለመግባት ፈቃድ እንዴት ማግኘት እችላሁ?

ሌላ የቪዛ ማቀነባበሪያ ጥያቄዎች

የቀጠሮ ተገኝነት

  1. ለወደፊት የተያዘ ቀጠሮ አለኝ ፣ ግን የሚያጥር ቀጠሮ ካለ እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ?
  2. የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ስሌለለ ፣ በሌላ አገር ለማመልከት መሞከር አለብኝ?
  3. የቀጠሮ ቀን ለማየት ወደ መለያዬ መግባት የምችልበት የተወሰነ የጊዜ ገደብ አለው?

ቀጠሮ መሰረዝ

  1. የቀጠሮ መሰረዝ ማስታወቂያ ከደረሰኝ በቀጠሮዬ መገኘት አለብኝ?
  2. ቀጠሮዬ ተሰርዟል። የማሳወቂያ ኢሜል ለምን አልደረሰኝም?
  3. ቀጠሮዬ ተሰርዞ እንደሆነ እንዴት ማወቅ እችላለሁ ፣ እና ከተሰረዘ ለምን ያህል ጊዜ ኢሜል ይደርሰኛል?

የቪዛ እድሳት

  1. ቪዛዬን ማደስ አለብኝ ፣ ግን ያለ ቃለ -መጠይቅ ለማደስ መግለጫዎችን አላየሁም። በቪዛ ቃለ መጠይቅ ላይ ላለመገኘት ብቁ የሚያደርጉን መግለጫዎች የት ማግኘት እችላለሁ?
  2. ለቪዛ እድሳት ምን ያህል ግዜ ይፈጃል?

አስቸኳይ ቀጠሮዎች

  1. የአስቸኳይ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ አቅርቤያለሁ ፣ ግን አሁንም መልስ እጠብቃለሁ
  2. የአስቸኳይ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄዬ ውድቅ ተደርጓል። ሌላ የአስቸኳይ ጊዜ ጥያቄ መላክ እችላለሁን?
  3. የአስቸኳይ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄዬ ተፈቅዶ ነበር ፣ ነገር ግን በአዲሱ የቀጠሮ ቀን ላይ መገኘት አልችልም

የቪዛ ክፍያዎች

  1. ቀጠሮ ለመያዝ የቪዛ ክፍያዬ ለምን ያህል ጊዜ ያገለግላል?
  2. የቪዛ ክፍያዬን ከፍዬ ነበር ፣ ነገር ግን የጉዞ እቅዶቼ ስለተለወጡ ፣ ቀጠሮዬ ብዙ ጊዜ ስለተሰረዘ ፣ ወይም ቀጠሮ ለማግኘት ረጅም የጥበቃ ጊዜ ምክንያት ቪዛ ማመልከቻዬ መቀጠል አልፈልግም ክፍያውን ተመላሽ ማድረግ እችላለሁ?

እየታዩ በሂደት ላይ ያሉ የቪዛ ማመልከቻዎች ሁኔታ

  1. ከብዙ ሳምንታት/ወራት በፊት የቪዛ እድሳት ማመልከቻዬን አስገብቼ የማመልከቻዬን ሁኔታ ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡
  2. ቪዛዬን ለማመልከትእና ስለ ቪዛ ማመልከቻዬ ሁኔታ ለማወቅ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

ሌላ

  1. መለያዬ ተዘግቷል የሚል ኢሜይል ደርሶኛል ፣ ምን ማድረግ እችላለሁ?
  2. በ 2020 የ DS-160 ፎርሜን ከሞላሁ ፣ በ 2021 ለቀጠሮዬ አዲስ ቅጽ መሙላት አለብኝ?

አጠቃላይ መረጃ

  1. የዚህ ድህረ ገጽ አላማ ምንድን ነው?

    እባክዎ በዚህ ድህረ ገጽ ለስደተኛ ቪዛ አመልካቾችና ለአሜሪካ ህጋዊ ቋሚ ነዋሪዎች ስለሚሰጡ አገልግሎቶች የበለጠ ለመረዳት የሚከተሉትን የመረጃ ገጾች ይጎብኙ፡

  2. የይለፍ ቃሌን እረሳሁ. የይለፍ ቃሌን እንዴት ዳግም መቀየር እችላለሁ?

    በ 'በመለያ ይግቡ ወይም ሒሳብ ይፍጠሩ' በሚለው ገጽ ላይ 'የይለፍ ቃልዎን ረሱ?' የሚለውን ይምረጡ። ከዚያ ከተጠቃሚ መለያዎ ጋር የተገናኘውን የኢሜል አድራሻ ያስገቡ። የይለፍ ቃልዎን እንደገና ለማስጀመር መመሪያዎችን የያዘ ኢሜይል እንልክልዎታለን።

  3. ወደ መለያዬ ለመግባት ጥቅም ላይ የዋለውን ኢሜይል እንዴት መቀየር እችላለሁ?

    የኢሜል አድራሻውን መቀየር የሚችለው የመለያው ባለቤት ብቻ ነው። የመለያው ባለቤት መጀመሪያ ወደ መለያው መግባት አለበት፣ ከዚያም በመረጃዎች በሚለው ሜኑ ስር ወደ ' የሀሂሳብ ቅንጅቶች' ይሂዱ እና ' “ወቅታዊ ኢሜል ይስጡ” የሚለውን ይምረጡ። ሶስተኛ ወገን መለያውን ከፈጠረው የኢሜል አድራሻውን ለመቀየር በቀጥታ እነሱን ማግኘት አለብዎት።

  4. የአሜሪካ ቪዛ ሳመለክት የማህበራዊ ሚድያ መለያየን እንዳሳውቅ የሚያዝ መመሪያ አለ ወይ?

    በግንቦት 13፣ 2011 ዓ.ም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ የነዋሪዎችና የአጭር ግዜ ቪዛ መጠየቂያ ፎርሞች ላይ ስለ የማህበራዊ ሚድያ መለያ ተጨማሪ ጥያቄዎች አካቷዋል፡፡ ይህ ተጨማሪ ጥያቄ በአጠቃላይ የትም አገር ላይ ሆነው የሚያመለክቱ አመልካቶችን ይመለከታል፡፡ ለበለጠ መረጃ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ተዘውትረው ሊሚጠየቁ ጥያቄዎች የሚሰጡትን መልሶች ይመለከቱ፡፡

የስደተኛ ቪዛ መረጃ

  1. የስደተኛ ቪዛ ምንድን ነው?

    የስደተኛ ቪዛ ወደ አሜሪካ በመጓዝ እንደ ህጋዊ ቋሚ ነዋሪ ለመግባት የሚያስችለውን ማመልከቻ ለማቅረብ የሚያስችል በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚሰጥ ሰነድ ነው፡፡ ተጨማሪ መረጃ በአሜሪካ የዜግነትና የስደተኛ አገልግሎቶች ድህረ ገጽ - United States Citizenship and Immigration Services (USCIS) - ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

  2. ለስደተኛ ቪዛ ለማመልከት የሚያስችል ማመልከቻ በእኔ ስም ገብቷል፤ ነገር ግን ማመልከቻው አሁንም በአሜሪካ የዜግነትና የስደተኛ አገልግሎቶች (USCIS) ይገኛል፤ ማመልከቻው ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ እንዴት ማጣራት እችላለሁ?

    ማመልከቻዎ ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ በአሜሪካ የዜግነትና የስደተኛ አገልግሎቶች (USCIS) ድህረ ገጽ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡

    ይህ ድህረ ገጽ እንዲሁም ተዛማጅ የጥሪ ማዕከል አገልግሎቶች በአሜሪካ የዜግነትና የስደተኛ አገልግሎቶች (USCIS) ስለገባ ማመልከቻ ተጨባጭ ሁኔታ መረጃ መስጠት አይችሉም፡፡

  3. ለስደተኛ ቪዛ ለማመልከት ምን ያህል ያስከፍላል?

    የክፍያዎች መጠን እንደቪዛው አይነት ይለያያል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/visa-information-resources/fees/fees-visa-services.html ይመልከቱ፡፡

የስደተኛ ቪዛ የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ

  1. ጉዳዬ በብሔራዊ የቪዛ ማዕከል (National Visa Center - NVC) ይገኛል፤ ይህንን ቢሮ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

    የብሔራዊ የቪዛ ማዕከልን (NVC) በኢሜይል https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/visa-information-resources/ask-nvc.html ማግኘት ይችላሉ፡፡ በሚልኩት መልዕክት ውስጥ የማመልከቻዎን ቁጥር(ቁጥሮች) እና የአመልካቹን ሙሉ ስም እስከነአያት ማካተትዎን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡

  2. ቀጠሮ እንደተያዘልኝ እንዴት አውቃለሁ?

    የብሔራዊ የቪዛ ማዕከል (National Visa Center - NVC), የኬንታኪ የቆንስላ ማዕከል (Kentucky Consular Center - KCC) ወይንም የኤምባሲው ቆንስላ ክፍል የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ እንደተያዘልዎ ለእርስዎ፣ ማመልከቻዎን ላስገባልዎ እንዲሁም ለጠበቃዎ የቃለ መጠይቅዎን ቀን፣ ሰዓትና ቦታ ያሳውቃል፡፡

    ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ ህጋዊ ቋሚ ነዋሪዎች የሚለውን ይመልከቱ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/immigrate/the-immigrant-visa-process/interview/interview-prepare.html.

  3. በቃለ መጠይቁ ወቅት ምን ይዤ መቅረብ ይኖርብኛል?

    ለቃለመጠይቅ ለመዘጋጀት እንዲመቾት ከ ኤን.ቪ. ሲ (NVC) ኬሲሲ (KCC) ወይም ከአሜሪካን ኤምባሲ ኮንስላር ክፍል የተላከሎትን ደብዳቤ ያንብቡ፡፡

  4. ቃለ መጠይቅ አድርዴ በአንቀጽ 221(g) መሠረት ተጨማሪ ሰነድ ወይንም መረጃ ምክንያት ተከልክያለሁ፡፡ ይህን ለማቅረብ አሁን ዝግጁ ነኝ - ይህንን እንዴት ለማድረግ እችላለለሁ? ወደ ኤምባሲው በድጋሚ መምጣት ይኖርብኛል?

    በቃለ መጠይቅዎ ወቅት የቆንስላ ኃላፊው የሰጠዎ ደብዳቤ ማመልከቻዎን እንዴት ማጠናቀቅ እንደሚገባዎ አስፈላጊውን መመሪያ ይሰጥዎታል፡፡ እባክዎ በደብዳቤው ላይ የሚገኙትን መመሪያዎች ይከተሉ፡፡

  5. የቃለ መጠይቅ ቀጠሮዬ ካመለጠኝ ወይንም ካለፈኝ ምን ማድረግ ይገባኛል?

    የቃለ መጠይቅ ቀጠሮዎት ካመለጥዎ፣ ወደ አካውንትዎ በመግባት "ቀጥል" የሚለውን ከዚያም "ቀጠሮዬ አመለጠኝ" የሚለውን በመምረጥ መመሪያዎችን ይከተሉ፡፡ ይኽንን ጥያቄ ለማቅረብ ከመጀምሪያ ቀጠሮ 24 ሰዓት መጠበቅ ይኖርቦታል፡፡

የቪዛ ጥቅል ሰነዶች እና ዘመናዊው የኢሚግራንት (የነዋሪነት) ቪዛ

  1. ጥያቄ፡ በቅርቡ የኢሚግራንት ቪዛ ቃለመጠይቅ አድርጌ ቪዛዬን ተረክቤአለሁ፡፡ ነገርግን አብሬ ይዤው የሚሄደው የታሸገ ፖስታ አልተሰጠኝም፡፡ ጠበቃዩ/ የሚወስደኝ ግለሰሰብ ወይም ጎደኞቼ ያለዚህ ፖስታ መብረር እንደሌለብኝ ነግረውኛል፡፡ ምን ማድረግ ነው ያለብኝ ?

    መልስ፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአንዳንድ የቪዛ አይነቶች አዲስ የኤሌክትሮኒክ አሰራር ጀምሯል፡፡ በናሽናል ቪዛ ሴንተር ወይም ቃለመጠይቅ ያደረጉበት ኤምባሲ የሲቪል ወይም የፋይናንስ ሰነዶችዎን በ CEAC ድህረገጽ በኤሌክትሮኒክ መንገድ እንዲልኩ ተጠይቀው ከነበረ ቪዛዎ በአዲሱ የኤሌክትሮኒክ መንገድ የተሰጦት ስለሆነ ከዚህ የተለየ ትዕዛዝ ወይም መረጃ ቃለመጠይቅ ካደረጉበት ኤምባሲ ካልደረስዎት በስተቀር ተጨማሪ የመግቢያ ወደብ ላይ የሚያሳዩት የታሸገ ፖስታ አያስፈልጎትም፡፡ ሰነድዎ ቀድሞ በኤሌክትሮኒክ መንገድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአገር ደህንነት ቢሮ የተላለፈ ስለሆነ ወድብ ላይ ያሉ የደህንነት መኮንኖች ሰነድዎን እዛው ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህ አዲስ የኤሌክትሮኒክ አሰራር ማመልከቻዎ በቀልጣፋ መንገድ እንዲስተናገድ ይረዳዎታል፡፡

  2. ጥያቄ፡ የሲቪል ወይም የፋይናንስ ሰነዶቼን በ CEAC ድህረገጽ በኤሌክትሮኒክ መንገድ ወይም በሌላ መንገድ ልላክ አላስታውስም ፡፡ ቪዛዬ በወረቀት አልባው አሰራር እንደተሠጠኝ ማወቅ የምችልበት መንገድ አለ ወይ ?

    መልስ፡ ይችላሉ ቪዛዎን ይመልከቱ ተቸማሪ ሰነድ የማያስፈልጎት ከሆነ ቪዛዎት ላይ በስተቀኝ ጫፉ ላይ በሚገኝ ፎቶዎት ላይ “IV DOCS in CCD”. የሚል ምልክት ያያሉ

  3. ጥያቄ፡ አንዳንድ ሰዎች በእጅ ተይዞ የሚገባ የታሸገ ፖስታ ሲሰጣቸው አውቃለሁ የኔ ከነሱ ለም ተለየ ?

    መልስ፡ ይህን አሰራር ስራ ላይ ማዋል የተጀመረው በ 2018 ዓ.ም ነው ፡፡ ሁሉንም የቪዛ አይነት በዚህ መንገድ ለመለወጥ የተወሰኑ ዓመታት ሊፈጅ ይችላል፡፡ ይህ አሰራር ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ እስኪውል የተወኑ አመልካቾች በእጅ ተይዞ የሚገባ የታሸገ ፖስታ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ እነዚህ አመልካቾች ቪዛቸው ላይ “IV DOCS in CCD”. የሚል ምልክት አይኖረውም፡፡

ህጋዊ ቋሚ ነዋሪ (የቋሚ ነዋሪነት መታወቂያ -ግሪን ካርድ – የያዙ)

  1. በቅርቡ የሚቃጠል የቋሚ ነዋሪነት መታወቂያ (ግሪን ካርድ) አለኝ፣ አዲስ መታወቂያ/ካርድም አልደረሰኝም፡፡ ወደ አሜሪካ እንዴት ተመልሼ መግባት እችላለሁ? ህጋዊነቴን አጥቻለሁ?

    አይ፤ ህጋዊነትዎን አላጡም፡፡ ነገር ግን ወደ አሜሪካ ተመልሰው ለመግባት እንዲችሉ ቦርዲንግ ፎይል ለማግኘት ማመልከት ይኖርቦታል፡፡

    ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ ህጋዊ ቋሚ ነዋሪዎች የሚለውን ይመልከቱ http://travel.state.gov/content/visas/en/immigrate/returning-residents.html፡፡

  2. የቋሚ ነዋሪነት መታወቂያ (ግሪን ካርድ) አለኝ፣ ነገር ግን ከአሜሪካ ውጪ ከአንድ ዓመት በላይ ቆይቻለሁ፡፡ ወደ አሜሪካ ተመልሼ ለመግባት ፈቃድ እንዴት ማግኘት እችላሁ?

    አመርካን ሀገር ውስጥ ለመግባት እንዲፈቀድልዎ የሚያደርግ ቪዛ እንዲሰጥዎ ለተመላሽ ነዋሪነት ቪዛ አንዲያመለክቱ ያስፈልጋል፡፡

    ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ ህጋዊ ቋሚ ነዋሪዎች የሚለውን ይመልከቱ http://travel.state.gov/content/visas/en/immigrate/returning-residents.html፡፡

ሌላ የቪዛ ማቀነባበሪያ ጥያቄዎች

የቀጠሮ ተገኝነት

  1. ለወደፊት የተያዘ ቀጠሮ አለኝ ፣ ግን የሚያጥር ቀጠሮ ካለ እንዴት ማረጋገጥ እችላለሁ?

    ቀጠሮ መኖሩን በንቃት ካልተከታተሉ በስተቀር አጭር ቀጠሮ ማግኘት አይችሉም። ቀጠሮ ይዘው የቀደመ ቀጠሮ የሚገኝ መሆኑን ለማየት ከፈለጉ በዚህ ድር ጣቢያ ላይ ወደ መለያዎ መግባት አለብዎት (https://ais.usvisa-info.com/) ፣ ቀጥል የሚለውን ቀጥሎም "ቀጠሮ ለሌላ ጊዜ ያስተላልፉ" ይምረጡ። በቀን መቁጠሪያ የሚታየው የቀጠሮ ቀን መቁጠሪያ በቪዛዎ አይነትና እና በሌሎች መመዘኛዎች ላይ በመመስረት የሚገኙ ቀጠሮዎችን ያጠቃልላል። የአሁኑን ቀጠሮዎን ለማቆየት ከመረጡ ፣ ዝጋ የሚለውን ይምረጡ።

  2. የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ስሌለለ ፣ በሌላ አገር ለማመልከት መሞከር አለብኝ?

    እርስዎ ዜጋ ወይም ህጋዊ ቋሚ ነዋሪ በሆኑበት ሀገር ውስጥ እንዲያመለክቱ እንመክራለን። በአሁኑ ጊዜ አብዛኛዎቹ የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች የቪዛ ማመልከቻዎችን ለማስተናገድ ውስን አቅም ስላላቸው ለዜጎች እና ለህጋዊ ቋሚ ነዋሪዎች ማመልከቻዎች ቅድሚያ ይሰጣሉ።

  3. የቀጠሮ ቀን ለማየት ወደ መለያዬ መግባት የምችልበት የተወሰነ የጊዜ ገደብ አለው?

    ወደ መለያዎ ለመግባት ምንም ገደብ የለውም ፤ ሆኖም ፣ በተራዘመ ጊዜ ውስጥ በስርዓቱ ውስጥ አንድ ገጽን በተደጋጋሚ ማደስ መለያዮ እንዲዘጋ ሊያደርግ ይችላል በተጨማሪም ፣ ይህንን ድር ጣቢያ በበርካታ ኮምፒተሮች በአንድ ጊዜ መግባት ወይም እንደ ቦቶች ወይም እስክሪፕቶች ያሉ አውቶማቲክ ወይም ሰው ያልሆኑ መንገዶችን መጠቀም በአጠቃቀም ውሉ መሰረት የተከለከለ ነው።

ቀጠሮ መሰረዝ

  1. የቀጠሮ መሰረዝ ማስታወቂያ ከደረሰኝ በቀጠሮዬ መገኘት አለብኝ?

    የቀጠሮ ስረዛ ማሳወቂያ ከተቀበሉ በቆንስላ ቀጠሮዎ ላይ መገኘት የለብዎትም። ቀጠሮዎን ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ፣ እባክዎን በዚህ ድር ጣቢያ (https://ais.usvisa-info.com/) ላይ ወደ የተጠቃሚ መለያዎ ይግቡ ፣ “ቀጥል” የሚለውን አማራጭ ይምረጡ እና በ “ቀጠሮ ቀጠሮ” አማራጭ ስር የስርዓት መመሪያዎችን ይከተሉ። ተጨማሪ እርዳታ ከፈለጉ እባክዎን በገጹ ታችኛው ክፍል ላይ ያለውን የእገዛ ክፍልን ይመልከቱ።

  2. ቀጠሮዬ ተሰርዟል። የማሳወቂያ ኢሜል ለምን አልደረሰኝም?

    ቀጠሮ ሲሰረዝ ፣ ስርዓቱ በቀጠሮ መርሐግብር ስርዓት ውስጥ በተመዘገበው የኢሜል አድራሻ ኢሜል ይልካል። አንዳንዴ የተመዘገበው የኢሜል አድራሻ ትክክል አይደለም ፣ አመልካቹ ያስመዘገበውን ኢሜይል ማየት አይችልም፣ ወይም ማሳወቂያው ወደ አላስፈላጊ ስፓም ወይም ጃንክ ይሄዳል። በእነዚህ ምክንያቶች አመልካቾች ወደዚህ ድር ጣቢያ (https://ais.usvisa-info.com/) በመግባት ከቀጠሮው አንድ ወይም ሁለት ቀናት በፊት የቀጠሮቸውን ሁኔታ እንዲመለከቱ እንመክራለን።

  3. ቀጠሮዬ ተሰርዞ እንደሆነ እንዴት ማወቅ እችላለሁ ፣ እና ከተሰረዘ ለምን ያህል ጊዜ ኢሜል ይደርሰኛል?

    በአጠቃላይ ፣ የቆንስላ ክፍሎች ቢያንስ ከሦስት ሳምንታት በፊት ቀጠሮዎችን ለመሰረዝ ይሞክራሉ። ሆኖም ፣ አሁን ካለው ተለዋዋጭ ሁኔታ አንፃር ፣ መሰረዙ ከቀጠሮው ከሦስት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሊከሰት ይችላል። በዚህ ድር ጣቢያ (https://ais.usvisa-info.com/) ውስጥ በመግባት አመልካቾች የቀጠሮውን ሁኔታ ከአንድ ወይም ሁለት ቀን በፊት እንዲፈትሹ እንመክራለን።

የቪዛ እድሳት

  1. ቪዛዬን ማደስ አለብኝ ፣ ግን ያለ ቃለ -መጠይቅ ለማደስ መግለጫዎችን አላየሁም። በቪዛ ቃለ መጠይቅ ላይ ላለመገኘት ብቁ የሚያደርጉን መግለጫዎች የት ማግኘት እችላለሁ?

    ለማደስ ብቁ መሆን አለመሆናቸው ይወሰናል፡፡ አማራጩ ካልቀረበሎት ወይም ብቁ ሆነው አልተገኙም፡፡ ወይ በሚያመለክቱበት በቆንስላ ክፍል ውስጥ ይህ አገልግሎት የለም፡፡

  2. ለቪዛ እድሳት ምን ያህል ግዜ ይፈጃል?

    እያንዳንዱ የቪዛ ማመልከቻ ልዩ በመሆኑ እና በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ በመመርኮዝ ስለሚታይ የሂደቱ ጊዜ ይለያያል። በተጨማሪም ፣ የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች በተወሰነ አቅም እየሠሩ ስለሆነ ፣ ይህም ቪዛዎን ለማግኘት ሊያዘገይ ይችላል። የቪዛ ማመልከቻዎን ሁኔታ በ https://ceac.state.gov/CEAC ላይ መከታተል ይችላሉ።

አስቸኳይ ቀጠሮዎች

  1. የአስቸኳይ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ አቅርቤያለሁ ፣ ግን አሁንም መልስ እጠብቃለሁ

    የቆንስላ ክፍሎች ብዛት ያላቸው የአስቸኳይ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄዎችን እያስተናገዱ ነው። በሰው ሀይል መገኘት ላይ በመመርኮዝ እነዚህ ጥያቄዎች ተገምግመው መልስ ይሰጣቸዋል። ለአስቸኳይ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄዎ ገና ምላሽ ካልተቀበሉ ፣ ተመሳሳይ ጥቄዎችን ለለመለስ በትጋት እየሠሩ ስለሆኑ እባክዎን ከቆንስላ ክፍሉ መልስ ይጠብቁ። ምላሽ ካልደረስዎ ፣ በቆንስላ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮዎ ላይ በመጀመሪያው ቀጠሮ ቀን እና ሰዓት ለመገኘት ያቅዱ።

  2. የአስቸኳይ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄዬ ውድቅ ተደርጓል። ሌላ የአስቸኳይ ጊዜ ጥያቄ መላክ እችላለሁን?

    በጣም ውስን በሆኑ ጉዳዮች፣ የተወሰኑ የቆንስላ ክፍሎች አመልካቾች ከአንድ ጊዜ በላይ የአጭር ቀጠሮ ጥያቄ እንዲያቀርቡ ሊፈቅዱላቸው ይችላሉ። ሌላ የአጭር ቀጠሮ ጥያቄ ለመላክ ፍቃድ እንዳለዎት ለማረጋገጥ በዚህ ድረ-ገጽ (https://ais.usvisa-info.com/) ላይ ወደ መለያዎ በመግባት ማየት ይእላሉ። አዲስ የተፋጠነ ጥያቄ ለማቅረብ አማራጭ ከሌልዎት፣ በተያዘሎት ቀን በቆንስላ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮዎ ላይ ለመገኘት ማቀድ አለብዎት።

  3. የአስቸኳይ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄዬ ተፈቅዶ ነበር ፣ ነገር ግን በአዲሱ የቀጠሮ ቀን ላይ መገኘት አልችልም

    በተፋጣኝ የቀጠሮ ጥያቄዎች ብዛት ምክንያት፣ የቆንስላ ክፍሎች የተወሰኑ የአደጋ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄዎችን ብቻ እያፀደቁ ነው። የአስቸኳይ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄዎ ተቀባይነት ካገኘ እና አዲስ ቀጠሮ ከተቀበሉ ፣ የቀጠሮ አቅም እጅግ በጣም ውስን ስለሆነ ለመገኘት ሁሉንም ጥረት እንዲያደርጉ እንመክራለን።

    በአስቸኳይ ጊዜ ቀጠሮዎ ላይ መገኘት ካልቻሉ ፣ቀጠሮውን መሰረዝ እና በሚገኘው ክፍት ቦታ አዲስ ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ።

የቪዛ ክፍያዎች

  1. ቀጠሮ ለመያዝ የቪዛ ክፍያዬ ለምን ያህል ጊዜ ያገለግላል?

    ይህ የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ከተገዛበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ዓመት ያህል ይሠራል። ሆኖም ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ብዙ የቪዛ አመልካቾች የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንደከፈሉ እና ቀጠሮ ለመያዝ እንደሚጠብቁ ተረድቷል። በዚህ ምክንያት ፣ ከውጭ ጉዳይ መምሪያ መመሪያ መሰረት የቪዛ ክፍያ እስከ ሴፕቴንበር 30 ቀን 2023 ተራዝሟል።

    የቪዛ ክፍያዎ የሚያበቃበትን ቀን ለመመልከት በዚህ ድር ጣቢያ (https://ais.usvisa-info.com/) ላይ ወደ መለያዎ ይግቡ ፣ ቀጥል የሚለውን መርጠው እና የክፍያ ደረሰኝ አማራጭን ይምረጡ። ለእያንዳንዱ አመልካች የቪዛ ክፍያ ማብቂያ ቀን በክፍያ ደረሰኝ ላይ ተዘርዝሯል።

  2. የቪዛ ክፍያዬን ከፍዬ ነበር ፣ ነገር ግን የጉዞ እቅዶቼ ስለተለወጡ ፣ ቀጠሮዬ ብዙ ጊዜ ስለተሰረዘ ፣ ወይም ቀጠሮ ለማግኘት ረጅም የጥበቃ ጊዜ ምክንያት ቪዛ ማመልከቻዬ መቀጠል አልፈልግም ክፍያውን ተመላሽ ማድረግ እችላለሁ?

    የቪዛ ክፍያዎች የማይመለሱ እና የማይተላለፉ ናቸው። ስደተኛ ያልሆኑ የቪዛ አመልካቾች ሁሉ ቀጠሮ ከመያዙ በፊት የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ መክፈል አለባቸው። የቪዛ ክፍያውን ከመክፈላቸው በፊት አመልካቾች የቪዛ ክፍያው ለቪዛ አመልካቹ እንደሚመደብ እና ክፍያው የማይመለስ ለሌላ ሰው የማይተላለፍ መሆኑን ወይም በሌላ ሀገር ውስጥ ለመጠቀም የማይተላለፍ መሆኑን (ሳጥኑ ላይ ምልክት በማድረግ) አምነው መቀበል ይጠበቅባቸዋል።

    ይህ የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ከተገዛበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ዓመት ያህል ይሠራል። ሆኖም ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ብዙ የቪዛ አመልካቾች የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ እንደከፈሉ እና ቀጠሮ ለመያዝ እንደሚጠብቁ ተረድቷል። በዚህ ምክንያት ፣ ከውጭ ጉዳይ መምሪያ መመሪያ መሰረት የቪዛ ክፍያ እስከ ሴፕቴንበር 30 ቀን 2023 ተራዝሟል።

    የቪዛ ክፍያዎ የሚያበቃበትን ቀን ለመመልከት በዚህ ድር ጣቢያ ላይ ወደ መለያዎ ይግቡ (https://ais.usvisa-info.com/) ፣ ቀጥል የሚለውን ይምረጡ እና የክፍያ ደረሰኝ አማራጭን ይምረጡ። ለእያንዳንዱ አመልካች የቪዛ ክፍያ ማብቂያ ቀን በክፍያ ደረሰኝ ላይ ተዘርዝሯል

እየታዩ በሂደት ላይ ያሉ የቪዛ ማመልከቻዎች ሁኔታ

  1. ከብዙ ሳምንታት/ወራት በፊት የቪዛ እድሳት ማመልከቻዬን አስገብቼ የማመልከቻዬን ሁኔታ ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡

    የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች በውሰን አቅም እየሠሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የቪዛ ማመልከቻዎችን ለማካሄድ የሚገኙ ውስን ሀብቶች ብቻ ናቸው። ስለዚህ ፣ የቪዛ ማመልከቻን ለማስኬድ እና የተፈቀደውን የአሜሪካን ቪዛ ለማተም የሚያስፈልገው ጊዜ ከተለመደው በላይ (በአንዳንድ ሁኔታዎች በርካታ ወሮች) ይወስዳል።

    የቪዛ እድሳት ሰነዶችዎን ካስገቡ ወይም በቪዛ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ላይ ከተገኙ በኋላ የቪዛ ማመልከቻዎን ሁኔታ በ https://ceac.state.gov/CEAC መከታተል ይችላሉ። የመረጃ ቡዱኑ ከዚህ የተለየ መረጃ ስለሌላቸው ስለ ማመልከቻዎ ሁኔታ ለመጠየቅ አይደውሉ ወይም ኢሜል አይላኩልን።

  2. ቪዛዬን ለማመልከትእና ስለ ቪዛ ማመልከቻዬ ሁኔታ ለማወቅ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

    እያንዳንዱ የቪዛ ማመልከቻ ልዩ በመሆኑ እና በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ በመመርኮዝ ስለሚታይ የሂደቱ ጊዜ ይለያያል። በተጨማሪም ፣ የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች በተወሰነ አቅም እየሠሩ ስለሆነ ፣ ይህም ቪዛዎን ለማግኘት ሊያዘገይ ይችላል። የቪዛ ማመልከቻዎን ሁኔታ በ https://ceac.state.gov/CEAC ላይ መከታተል ይችላሉ።

ሌላ

  1. መለያዬ ተዘግቷል የሚል ኢሜይል ደርሶኛል ፣ ምን ማድረግ እችላለሁ?

    በዚህ ድረገጽ ጣቢያ ላይ ወደ መለያዎ ይግቡ (https://ais.usvisa-info.com/) እና የመለያ መልሶ ማስከፈትን በተመለከተ የተሰጡትን መመሪያዎች ይከተሉ።

  2. በ 2020 የ DS-160 ፎርሜን ከሞላሁ ፣ በ 2021 ለቀጠሮዬ አዲስ ቅጽ መሙላት አለብኝ?

    የተሞሉ DS-160 ቅጾች ጊዜያቸው አያልፍም። በቅጹ ላይ የገባው መረጃ አሁንም ትክክል ከሆነ ከብዙ ወራት በኋላ ለቪዛ ለማመልከት ሊያገለግሉ ይችላሉ። የተጠቀሙት ፎቶዎችም ተመሳሳይ ነው። አዲስ ፎቶ መጠቀም የሚኖርቦት ከሆነ የቪዛ ማመልከቻው በሚታይበት ወቅት ይጠየቃሉ፡፡