ማስታወቂያዎች

Update: Validity of the Nonimmigrant Visa Fee (MRV Fee)

11 ኦክቶበር, 2023

ከኦክቶበር 1፣ 2022 በፊት የተከፈሉ የቪዛ ((MRV Fee) ክፍያ በሙሉ በሴፕቴምበር 30፣ 2023 አገልግሎታቸው አብቀቷል ። የዚህ ክፍያ የአገልግሎት ግዜ የሚራዘም አይሆንም ፡፡ አመልካቾች እንደአዲስ ክፍያውን መክፈል እንዳይኖርባቸው ከሴፕቴምበር 30፣ 2023 በፊት ቀጠሮ ማስያዝ ወይም የቪዛ ማሳደሻ ጥያቄአቸውን ማቅረብ ነበረባቸው፡፡ ክፍያውን በ ከኦክቶበር 1፣ 2022 እና ከዚያ በኃላ ከከፈሉ ቀጠሮዎን ከከፈሉበት ቀን በአንድ አመት ግዜ ውስጥ ቀጠሮ ማስያዝ ነበረቦት ፡፡ እባክዎን ልብ ይበሉ ቃለ-መጠይቁ ራሱ በአንድ አመት ውስጥ መከናወን አያስፈልገውም ነገር ግን የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ በአብድ አመት ውስጥ መያዝ አለበት፡፡ | በተጨማሪም፣ ቀጠሮ ለመያዝ ከኦክቶበር 1፣ 2022 በፊት የተከፈለ የMRV ክፍያዎችን የሚጠቀሙ አመልካቾች የቀጠሮ ቀናቸውን ከኦክቶበር 1 ቀን 2023 በኋላ ለመቀየር እንዳይሞክሩ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል ይህን ካደረጉ የቀጠሮ ቀኑ ተሰርዞ እና የ MRV ክፍያውን ከአገልግሎት ውጭ ይሆናል።

ከኮቪድ-19 ክትባት እና የአሜሪካ ጉዞ

5 ሴፕተምበር, 2023

ስደተኛ ያልሆነ (የጉብኝት ቪዛ) ያላቸው መንገደኞች ወደ አሜሪካ ለመብረር ተቀባይነት ባለው የኮቪድ-19 ክትባት ሙሉ ለሙሉ መከተባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማሳየት አያስፈልጋቸውም። ለበለጠ መረጃ፡ https://wwwnc.cdc.gov/travel/page/before-travel ን ይጎብኙ።

የስደተኛ ቪዛ ( የመኖሪያ ቪዛ አመልካቾች፡ የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ህግ የስደተኛ ቪዛ አመልካቾች የስደተኛ ቪዛ ከመሰጠቱ በፊት የተወሰኑ ክትባቶችን እንዲወስዱ ይጠይቃል። ለበለጠ መረጃ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/immigrate/vaccinations.html ን ይጎብኙ።

ስለ ቪዛ ክፍያዎ የአገልግሎት ግዜ ጠቃሚ መረጃ

10 ጁላይ, 2023

የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ከተከፈለበት ቀን ጀምሮ ለ 365 ቀናት ጥቅም ላይ ይውላሉ። ከ 365 ቀናት በኋላ አመልካቹ የቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ካላስያዘ ወይም ለአሜሪካ ስደተኛ ያልሆነ ቪዛ (የኬ እጮኛ ቪዛን ጨምሮ) ለማመልከት ማመልከቻውን ካላቀረበ ክፍያው የአገልግሎት ግዜ አብቅቶ አመልካቹ ክፍያውን የመጠቀም መብቱን ያጣል። ነገር ግን በ2020 መጀመሪያ ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት መደበኛ የቆንስላ ስራዎች በመቋረጡ እና የዩኤስ ስቴት ዲፓርትመንት ሁሉንም መደበኛ የቪዛ ስራዎችን በተቻለ ፍጥነት እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ነበረበት ለመመለስ ባደረገው ጥረት ምክንያት መምሪያው የቪዛ ማመልከቻ ክፍያዎችን የአገልግሎት ግዜ አራዝሟል። በዚህም መሰረት ከፌብሩዋሪ 20፣ 2020 እስከ በሴፕቴምበር 30፣ 2022 መካከል የሚቃጠሉን ክፍያዎች። እስከ ሴፕቴምበር 30፣ 2023 አራዝሟል።

እባክዎ የቪዛ ክፍያዎን የአገልግሎት ግዜ ያረጋግጡ እና የሚከተሉትን ጠቃሚ መረጃዎች ያንብቡ።

  • የቪዛ ክፍያዎ የሚያበቃበትን ቀን ለማየት በዚህ ድህረ ገጽ (https://ais.usvisa-info.com/) ወደ መለያዎ ይግቡ፣ ቀጥል የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ እና የክፍያ ደረሰኝ ተመልከትን ይምረጡ። ለእያንዳንዱ የቪዛ አመልካች የቪዛ ክፍያ የሚያበቃበት ቀን በክፍያ ደረሰኙ ላይ ያገኛሉ።
  • ክፍያው ከማብቃቱ በፊት ክፍያውን ካልተጠቀሙበት ለቪዛ ማመልከት ከፈለጉ አዲስ ክፍያ መክፈል ይኖርብዎታል። በማለቂያው ቀን እስከ 23:59 EST ጊዜ ድረስ የቪዛ ክፍያን መጠቀም ይችላሉ።
  • የቪዛ ክፍያዎን ለወደፊቱ ቀጠሮ ለመያዝ (ከቪዛ ክፍያው ማብቂያ ቀን በኋላ) አዲስ የቪዛ ክፍያ ካልከፈሉ በስተቀር መጠቀም አይችሉም ክፍያው ካለቀበት ቀን በኋላ ቀጠሮህን መሰረዝ ወይም ሌላ ቀጠሮ መቀየር አይቻልም። የቪዛ ቃለመጠይቅ ቀጠሮ የክፍያ ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ የተያዘ ቢሆንም ቀጠሮዎ አሁንም የሚሰራ ነው። እባክዎ በተያዘለት የቪዛ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮዎ ላይ ለመገኘት ያቅዱ።
  • የቪዛ ክፍያ ጊዜው ካለፈበት ቀን በኋላ ቀጠሮዎን መሰረዝ ወይም ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ አይችሉም። ቀጠሮዎን ለመሰረዝ ወይም ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ከሞከሩ የመርሃግብር ስርዓቱ የመጀመሪያ ቀጠሮ የቪዛ ክፍያዎ ጊዜው ያለፈበት መሆኑን የሚያመለክት የማስጠንቀቂያ መልእክት አሳይቶ ቀጠሮዎን መሰረዝ ወይም ሌላ ቀጠሮ መቀጠል ከፈለጉ ስርዓቱ አዲስ የቪዛ ክፍያ እንዲከፍሉ ይጠይቆታል።
  • የቃለ መጠይቅ ቀጠሮዎን ካመለጠዎት እና ቀጠሮውን ለማስያዝ የሚውለው ክፍያ ቀድሞውኑ ካለፈ፣ በቪዛ ማመልከቻዎ መቀጠል ከፈለጉ አዲስ የቪዛ ክፍያ መክፈል ይኖርብዎታል። አዲስ ክፍያ ላለመክፈል በተያዘለት የቪዛ ቃለ መጠይቅ ቀጠሮ ቀጠሮ ላይ ለመገኘት ያቅዱ።
  • በቆንስላ ቀጠሮዎ ላይ ከተገኙ ነገር ግን በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ህግ አንቀፅ 221(ሰ) መሰረት ውድቅ ከተደረጉ እና የቪዛ ማመልከቻዎ ገና በመጠባበቅ ላይ ከሆነ፣ ቀጣይ ቀጠሮ ካስፈለጎት የቪዛ አመልካቹ ቀድሞውኑ ለቃለመጠይቅ ስለገባ በቪዛ ክፍያ ማብቂያ ቀን ላይ ተጽዕኖ አይደርስብዎትም። በቃለ መጠይቅዎ ወቅት የተቀበሉትን መመሪያዎች መከተል አለብዎት.

የቪዛ ክፍያዎን እና ቀጠሮዎን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እባክዎ https://ais.usvisa-info.com/ ላይ ያለውንመረጃ ይመልከቱ።

ስደተኛ ያልሆኑ ( የጉብኝት) ቪዛ ክፍያ

17 ጁን, 2023

  • ለንግድ ወይም ቱሪዝም የጎብኚ ቪዛዎች (B1/B2s እና BCCs) እና ሌሎች አቤቱታ-ያልሆኑ ቪዛዎች እንደ የተማሪ እና የልውውጥ የጎብኚ ቪዛ $185 ዶላር
  • ለጊዜያዊ ሰራተኞች (H, L, O, P, Q እና R ምድቦች) ለተወሰኑ አቤቱታ-ተኮር ስደተኛ ያልሆኑ ቪዛዎች የማመልከቻ ክፍያ $205 ዶላር
  • በልዩ ሙያ (ኢ ምድብ) ውስጥ ላሉ የስምምነት ነጋዴ፣ የስምምነት ባለሀብት እና የስምምነት አመልካች የማመልከቻ ክፍያ $315 ዶላር

ቀደም ሲል የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ አሁን የሚሰራ እና ጊዜው ያላለፈ ነገር ግን ለቪዛ ቃለመጠይቁ ገና ያልቀረቡ ወይም ጉዳያቸው እስኪታይ እየጠበቁ ያሉ አመልካቾች ምንም ተጨማሪ ክፍያ አይጠየቁም። ቀደም ሲል የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ የከፈሉ አመልካቾች ክፍያው ያልተቃጠለ እስከሆነ ድረስ እና ለቀለመጠይቅ ገና ያልገቡ አመልካቾች ከሆኑ ምንም ተጨማሪ ክፍያ አይከፍሉም

በዚህ ድህር ጣቢያ ላይ ስላለው የመለያዎ ግላዊነት እና ደህንነት ጠቃሚ መረጃ

30 ሜይ, 2023

የእርስዎ ግላዊነት እና ደህንነት አስፈላጊ ናቸው። ለዚህ ድህረ-ገጽ የመግቢያ መረጃዎትን ከማንም ጋር በምንም አይነት ሁኔታ እንዳያጋሩ አጥብቀን እንመክራለን። ቡድናችን የእርስዎን መረጃዎች በስልክም ሆነ በኢሜል በጭራሽ አይጠይቅም። መረጃዎትን ማጋራት የግል መረጃዎን አላግባብ መጠቀምን ወይም መጎዳትን ሊያስከትል ይችላል። በተጨማሪም፣ በዚህ ድህረ-ገጽ ውስጥ እንደ ቦቶች፣ ስክሪፕቶች ወይም ሌሎች ሰው ያልሆኑ በይነገጾች ያሉ አውቶማቲክ መሳሪያዎችን መጠቀም የተከለከለ ነው። እንደነዚህ ያሉ መሳሪያዎች የግል ውሂብዎን ትክክለኛነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ብቻ ሳይሆን የመተግበሪያዎን ሂደት መዘግየትንም ሊያስከትሉ ይችላሉ። ለተጨማሪ ዝርዝሮች የዚህን ጣቢያ የግላዊነት ፖሊሲ እና የአጠቃቀም ውሎች ይመልከቱ። ከፍተኛ የደህንነት እና የግላዊነት ደረጃን ለመጠበቅ ላደረጉት ትብብር እናመሰግናለን።

16 ሴፕተምበር, 2020

ለቪዛ አመልካቾች የወጣ አስቸኳይ መረጃ

ከቪዛ ጋር በተያያዘ ቀጠሮ ከመያዞ ወይም ከመቅረብዎ በፊት እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን መረጃ ይመልከቱ

ለተወሰኑ ስደተኛ ላልሆኑ ቪዛዎች የቃለ መጠይቁን መስፈርትነ በተመለከተ ላይ ጠቃሚ መረጃ

ስለ ቪዛ ክፍያዎ የአገልግሎት ግዜ ጠቃሚ መረጃ

በዚህ ድህር ጣቢያ ላይ ስላለው የመለያዎ ግላዊነት እና ደህንነት ጠቃሚ መረጃ

ከኮቪድ-19 ክትባት እና የአሜሪካ ጉዞ

ስደተኛ ያልሆኑ ( የጉብኝት) ቪዛ ክፍያ


U.S. Visa and Travel Updates

For the latest information from the U.S. Department of State regarding visa issues and travel to the United States, please visit: https://travel.state.gov/content/travel/en/News/visas-news.html.

ተጨማሪ የቪዛ መረከቢያ እና ሰነዶች መላኪያ ቅርንጫፎች

22 ኦገስት, 2018

አዲስ አበባ ከሚገኘው ሁለት የቪዛ መረከቢያ እና ሰነዶች መላኪያ ቅርንጫፎች በተጨማሪ ሁለት አዳዲስ የመላኪያ እና መላኪያ ቅርንጫፎች በመቀሌ እና ሐዋሳ መጨመራችንን በደስታ እንገልጻለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን ድህረገፅ ይጎብኙ፡፡ https://ais.usvisa-info.com/am-et/niv/information/courier_dropboxes