የስደተኛ ቪዛ አጠቃላይ እይታ

ወደ አሜሪካ ለመሰደድ ወይንም በቋሚነት ለመኖር የሚፈልጉ የውጭ ሀገር ዜጎች ለስደተኛ ቪዛ ለማመልከት የተለዩ ስልቶችን ወይንም ሥርዓቶችን መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ የስደተኛ ቪዛ በአሜሪካ የቆንስላ ክፍል የሚሰጥ ወደ አሜሪካ እንዲጓዙና እንደ ህጋዊ ቋሚ ነዋሪ እንዲገቡ ያስችልዎታል፡፡ አንዴ ከገቡ በኋላ በአሜሪካ በቋሚነት የመኖርና የመስራት መብት ይኖርዎታል፡፡ ተጨማሪ መረጃ በአሜሪካ የዜግነትና የስደተኛ አገልግሎቶች ድህረ ገጽ - United States Citizenship and Immigration Services (USCIS) ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡

ሂደቱን በራስዎ መጀመር አይችሉም፤ እናም የተፈቀደ ማመልከቻ (ፔቲሽን) ሊኖርዎት ይገባል፡፡ ማመልከቻ (ፔቲሽን) እንዴት ማስገባት እንደሚቻል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የአሜሪካ የዜግነትና የስደተኛ አገልግሎቶች - USCIS ድህረ ገጽ ይመልከቱ፡

የስደተኛ ቪዛ ሂደት

በስደተኛ ቪዛ ሂደት ማመልከቻውን ለማጠናቀቅ ብዙ እርምጃዎች ያስፈልጋሉ፡፡ የሂደቶቹ ዝርዝር በhttps://travel.state.gov ይገኛል፡፡ ከዚህ በታች የሚገኙት እርምጃዎች በአሜሪካ የዜግነትና የስደተኛ አገልግሎቶች (USCIS) ማመልከቻ ማስገባትዎን እንደ ቅድመ ሁኔታ ታሳቢ ያደረጉ ናቸው፡፡

ኃላፊነትን ስለመወሰን፡ ይህ ድህረ ገጽ እና ተዛማጅ የጥሪ ማዕከል አገልግሎቶች በአሜሪካ የዜግነትና የስደተኛ አገልግሎቶች (USCIS)፣ በብሔራዊ የቪዛ ማዕከል (National Visa Center - NVC), በኬንታኪ የቆንስላ ማዕከል (Kentucky Consular Center - KCC) ወይንም በኤምባሲው የቆንስላ ክፍል ስላሉ ሂደቶች ተጨባጭ ሁኔታም ይሁን መረጃ መስጠት አይችሉም፡፡

አንደኛ እርምጃ - የገባ ማመልከቻ (የUSCISን ፈቃድ የሚጠብቅ)

የገባውን የስደተኛ ማመልከቻ ተጨባጭ ሁኔታ በUSCIS wድህረ ገጽ ይመልከቱ፡፡


ሁለተኛ እርምጃ - የተፈቀደ ማመልከቻ

ከ ዩ.ኤስ.ሲ.አይ.ኤስ የነዋሪነት ቪዛ ጥያቄዎ ተቀባይነት አግኝቶ ወደ ናሽናል ቪዛ ሴንተር እንደተመራ የሚገልፅ ማታወቂያ ከደረስዎት ይህንን ድህረገፅ https://travel.state.gov/content/visas/en/immigrate/immigrant-process/approved.html በመጎብኘት ስለሚካሄዱ ቀጣይ ሂደቶች መገንዘብ ይችላሉ https://travel.state.gov/content/visas/en/immigrate/immigrant-process/approved/contact.html፡፡

የ ዳይቨርሲቲ (ዲቪ) ፕሮግራም የሚተዳደረው በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኬንታኪ ኮንስላር ሴንተር (ኬሲሲ) ነው ለበለጠ መረጃ ይህንን ድህረገፅ ይጎንኙ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/immigrate/diversity-visa-program-entry/diversity-visa-instructions.html፡፡

የብሔራዊ የቪዛ ማዕከል (NVC), የኬንታኪ የቆንስላ ማዕከል (KCC) ወይንም የኤምባሲው የቆንስላ ክፍል ተጨማሪ እርምጃዎችን እንዲሁም የቃለ መጠይቅ ቀን(ቀናት) የሚመለከቱ ማስታወቂያዎችን እንዲሁም መመሪያዎችን ይሰጣል፡፡


ሶስተኛ እርምጃ - ለቃለ መጠይቅ መዘጋጀት

ማስጠንቀቂያ፡ ስለ የነዋሪነት ቪዛ የቀጠሮ ደብዳቤ ወይም ኢሜል ካልደረስዎት በዚህ ድህረገጽ ላይ ለለመመዝገብ ገና ጊዜዎት አልደረሰም ማለት ነው፡፡ (እባክዎ ከዚህ በላይ የሚገኙትን አንደኛና ሁለተኛ ሂደቶች ይመልከቱ፡፡)

ለቃለ መጠይቅ ስለመዘጋጀት ለመረዳት እዚህ ይጫኑ፡፡

ከ ኤን.ቪ. ሲ (NVC) ኬሲሲ (KCC) ወይም ከአሜሪካን ኤምባሲ ኮንስላር ክፍል የቀጠሮ ደብዳቤ ወይም ኢ-ሜል ከደረሶት እዚህ ድህረገፅ ላይ ከቀጠሮ በፊት መመዝገብ ይኖርቦታል፡፡ ከዚህ በታች ይመልከቱ፡

የቀጠሮ ደብዳቤ ወይም ኢ-ሜል የደረሳቸው የነዋሪነት ቪዛ አመልካቾች በሙሉ፤ በዚህ ድህረገፅ ላይ አዲስ አካውንት መፍጠር ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የከፈቱት አካውንነት ካለ በ (/am-et/iv/users/sign_in.iv) በመግባት ይቀጥሉ፡፡


አራተኛ ሂደት - ለቆንስላ ክፍል ቀጠሮዎ መገኘት

ከ ኤን.ቪ. ሲ (NVC) ኬሲሲ (KCC) ወይም ከአሜሪካን ኤምባሲ ኮንስላር ክፍል የቀጠሮ ደብዳቤ ላይ በተገለፀው መሰረት በቀጠሮ ቀን ለቃለ መጠይቅ ይገኙ፡፡ እባክዎ የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በሙሉ ይዘው መቅረብ አይዘንጉ፡፡


አምስተኛ እርምጃ - ከቀጠሮዎ በኋላ

በአሜሪካ ቆንስላ ክፍል ቀጠሮዎ ከተገኙ በኋላ የቪዛ ማመልከቻዎን ተጨባጭ ሁኔታ በ https://ceac.state.gov/CEAC መከታተል ይችላሉ፡፡

የቪዛ ማመልከቻዎ ከተፈቀደ (እባክዎ https://ceac.state.gov/CEAC ይመልከቱ) የሰነዶችዎን በፖስታ አገልግሎት መመለስ በዚህ ድህረ ገጽ መከታተል ይችላሉ፡፡ እባክዎ በመለያ ይግቡ.