የጥገኛ (ቪ92) ወይም የስደተኛ (ቪ93) ተከታይ ቤተሰብ

የጥገኛ ወይም የስደተኛ ፍቃድ በአሜሪካ የተሰወጠው ግለሰብ (አመልካች) ባለቤቱን/ ባለቤትዋን ወይም እና ያላገቡ ልጆቻቸውን ዩናይትድ ስቴትስ ለመውሰድ ማመልከት ይችላሉ፡፡ I-730 ፎርም በጥገኛ የቤተሰብ አባል የተሞላላቸው የጥገኛ ተከታይ በመባል የሚታወቁ ሲሆን I-730 ፎርም በስደተኛ የቤተሰብ አባል የተሞላላቸው የስደተኛ ተከታይ በመባል ይታወቃሉ፡፡

የጥገኛ ወይም የስደተኛ ተከታይ ሆነው ከኮንስላር ክፍሉ በዚህ ድህረገፅ አማካኝነት ቀጠሮ እንዲይዙ ወይም እንዲያስመዘግቡ መመሪያ ከደረስዎት እባክዎ አዲስ አካውንት ይክፈቱ፣ ከዚህ ቀደም የከፈቱት አካውንት ካለ በመለያዎት ይግቡ፡፡

ስለ ጥገኛ (ቪ92) ወይም ስደተኛ (ቪ93) ተከታይ ቤተሰብ ተጨማሪ መረጃ በሚከተለው ድህረ ገፅ ማግኘት ይቻላል https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/immigrate/follow-to-join-refugees-and-asylees.html