የአሜረካ ስደተኛ ላልሆኑ የቪዛ ፈርጆች

መግለጫ

ስደተኛ ላልሆኑ ቪዛዎች ወደ አሜሪካ በጊዜያዊ ጉብኝት ፣ ለንግድ ፣ ለጊዜያዊ ስራ ፣ ለትምህርት ወይም ለህክምና ለሚሄዱ የሚሆን ነው። ለተሟላ የዩ.ኤስ. የጉዞ እና የቪዛ መረጃ እባክዎ https://travel.state.gov ይጎብኙ፡፡

እባክዎ ጉዞዎን ቀደም ብለው ያቅዱ። መንገደኛው ትክክለኛ ቪዛ እስከሚያገኝ ድረስ የአውሮፕላን ትኬት እንዳይቆርጥ አጥብቆ ይመከራል። በቪዛ ማመልከቻ ቃለመጠይቅ ወቅት ትኬት አያስፈልግም።

ቪዛ አሜሪካ ለመግባት ዋስትና እንደማይሆን ሁሉም መንገደኞች ማወቅ ይገባቸዋል። የሆምላንድ ደህንነት ክፍል(DHS) መግባትን ሊከለክል እንዲሁም በአሜሪካ የሚቆዩበትን ጊዜ ሊወስን ይችላል። ወደ አሜሪካ ስለመግባት ተጨማሪ መረጃ በhttps://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/visa-information-resources/all-visa-categories.html ማግኘት ይቻላል፡፡


የጉብኝት ቪዛ ፈርጆች

(B) ጉብኝት: ለንግድ ፣ ለጉብኝት ፣ ለህክምና

የጉብኝት ቪዛ ስደተኛ ላልሆኑ ቪዛ ሆኖ ሰዎች ወደ አሜሪካ በጊዜያዊነት ለንግድ (B1)፣ የሙያ አውደ ጥናቶችን ወይም ስበሰባዎችን ፣ ለመዝናናት ይጨምራል ፣የእረፍት ጊዜ ገዞ ወይም ቤተሰብ መጎብኘት ወይም ህክምናን ጨምሮ(B2),ወይም ሁለቱንም ቅልቅል(B1/B2) አለማዎች እሰከ ስድስት ወራት ጊዜ

(C) ወደ ሌላ ሀገር ለመሄድ አሜሪካን እንደ መሸጋገሪያ

በሁለት የውጭ ሀገራት መካከል በሚጓዙበት ጊዜ እንደ ጉዞው አካል በአሜሪካ ጉዞ ግንኙነት (ኮኔክሽን) ማድረግ ያለባቸው ግለሰቦች

 • የቡድን አባልወደ አሜሪካ እንደ መንገደኛ ወደ መርከብም ሆነ አውሮፕላን ለመቀላቀል እየተጓዘ ከሆነ የመሸጋገሪያ ቪዛ ያስፈልጋዋል። እባክዎን በረራ ወይም መረከበኛ ቡድን አባል ቪዛ መረጃ ይመልከቱ።
 • በውጭ ሀገር ወደብ ላይ በትልቅ የምቾት መንገደኛ ማጓጓዠ መርከብ ወይም ሌላ የጭነት መረከብ ከአሜሪካ ወጭ ወደሌላ የውጭ ሀገር እየተጓዘ ያለ፣ በጉዞው ወቅት የአሜሪካን ወደብ ቢጠቀም ፣ የሽግግር ቪዛ ወይም ስደተኛ ላልሆነ ቪዛ ያስፈልገዋል።

የትምህርት ቪዛ ፈርጆች

(F/M) መደበኛ ትምህርት ተማሪ ወይም የቋንቋ ተማሪ / የሙያ ትምህርት ወይመ መደበኛ ያለሆነ ትምህርት ተማሪ

ባጠቃለይ፣ ማንኛውም በተፈቀዱ ትምህርታዊ ክፍሎች ለማጥናት ወደ አሜሪካ የሚመጣ የቪዛ አመልካች የተማሪ ቪዛ ያስፈልገዋል።

በአሜሪካ ትምህርት ቤቶች ተቀባይነት እንደተገኘ ተማሪው ለመግባት ይዘጋጃል፣ በተማሪ እና ልውውጥ ጉብኝት የመረጃ ስርዓት ውሰጥ ይመዘገባል። ስለ SEVIS I-901 ክፍያ እና ተያያዥ ፊረማዎች በSEVIS ስርዓት ውስጥ እንዴት እንደሚሞላ መመሪያዎች በአሜሪካ ት/ቤት ይሰጣሉ። ት/ቤቱ የዋናው አመልካች እና ማንኛውም የቤተሰብ አባል ከዋናው አመልካች አስፈላጊውን I-20 ቅጽ(ቅጾች) ለማስወጣት አብረው ለመጓዝ ያቀዱትን ስም ጨምሮ በSEVIS ስርዓት ውስጥ ይመዘገባሉ። እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ የሆነ I-20 ይቀበላል። የቤተሰቡ አባለት ከዋናው አመልካች ጋር ካላመለከቱ ፣ የዋናውን I-20 በዋነው የቪዛ ያዥ ት/ቤት የተሰጠውን ቅጅ ያስፈልጋል። በበለጠ ለመረዳት የስደተኞች እና ጉምሩክ አስተዳደር (ICE) ተማሪ እና የልውውጥ ጉብኝት መርሃግብር (SEVP) ድህረገጽ ይመልከቱ ።

ቀጣይ ተማሪዎች የተማሪነት ደረጃቸውን እስቀጠበቁ ድረስ እና የSEVIS (http://www.ice.gov/sevis/) መዝገበቸው የወቅቱ ከሆነ በማንኛውም ጊዜ ቪዛ ማመልከት ይችላሉ። ቀጣይ ተማሪዎቸ የክፍል ትምህርታቸው ከመጀመሩ በፊት በማንኛውም ጊዜ አሜሪካ መግባት ይችላሉ።

(J) የልውውጥ ጎብኝ

ልውውጥ ጎብኝ(J-1) ቪዛዎች ስደተኛ ያልሆኑ ቪዛዎች ሆነው በአሜሪካ የልውውጥ መርሃግብር ለመሳተፍ የተፈቀደላቸው ግለሰቦች የሚሰጥ ነው። ስለመርሃግብሩ መስፈርቶች ፣ ደንቦች እና የበለጠ ለማወቅ የመንግስት ክፍሉን J-1 ቪዛ ልውውጥ ጉብኝት መርሃግብር ድህረገጽ በ http://j1visa.state.gov/programs ይጎብኙ።

በአሜሪካ የልውውጥ ጉብኝት መረኃግብር ተቀባይነት እንዳገኘ ተጓዡ በተማሪ እና ልውውጥ ጉብኝት መረጃ ስርዓት (SEVIS) ውስጥ ይመዘገባል። አብዛኞቹ የJ-1 የልውውጥ ጎብኝዎች የSEVIS I-901 ክፍያ መክፈል አለባቸው። (የ J-1 ልውውጥ ጉብኝት መረኃግብር ባለቤት እና/ወይም ልጆች ከጎብኝው ጋር አብረው እንዲጓዙ ከፈቀደ፣ የቤተሰቡ አባላት ይህንን ክፍያ እንዲከፍሉ አይጠበቅባቸውም።) የመርሀግብሩ ድጋፍ ሰጭ የልውውጥ ጎብኝውን DS-2019 ቅጽ በቪዛ ቃለመጠይቁ እንዲያቀርበው ይሰጠዋል። በመርሀግበሩ ባለቤትዎ ወይም ልጆቸዎ እንዲሳተፉ የመፈቅድ ከሆነ ፣ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባላት የራሳቸው የሆነ DS-2019 ቅጽ ይሰጣቸዋል ለJ-2 ቪዛዎች እንዲያመለክቱ። SEVIS እና SEVIS I-901 ክፍያ በበለጠ ለመረዳት የስደተኞች እና ጉምሩክ አስተዳደር (ICE) ተማሪ እና የልውውጥ ጉብኝት መርሃግብር (SEVP) ድህረገጽ ይመልከቱ።


የስራ ቪዛ ፈርጆች

(D) የቡድን አባል

የነጂዎችና የመስተንግዶ ቡድን አባላት (Crewmember) (D) ቪዛዎች በአሜሪካ ባሉ መርከቦች (ለምሳሌ የሽርሽር ወይንም የዓሳ አጥማጅ መርከቦች) ወይንም አለም አቀፍ አየር መንገዶች ላይ ለሚሰሩ የሚሆኑ ስደተኛ ያልሆኑ ቪዛዎች ናቸው፤ የሰራተኞቹም ቅጥር ለእለት ከእለት ስራዎችና የአገልግሎት አሰጣጥ አስፈላጊ ነው፡፡

የነጂዎችና የመስተንግዶ ቡድን አባላት (Crewmember) (D) ቪዛ የሚያስፈልጋቸው የጉዞ ዓላማዎች፡

 • የመንገደኞች አውሮፕላን አብራሪ ወይንም አስተናጋጅ
 • በመርከብ ላይ የሚሰሩ ካፒቴን፣ ኢንጂነር ወይንም ሌሎች መርከበኞች
 • በሽርሽር መርከብ ላይ የሚሰሩ የነፍስ አድን ሰራተኛ፣ የምግብ ባለሙያ፣ አስተናጋጅ፣ የውበት ባለሙያ እና ሌሎች የአገልግሎት ሰራተኞች
 • በመርከብ ላይ የሚገኙ ሰልጣኞች

አመልካቹ ወደ የሚሰራበት መርከብ ለማግኘት እየሄደ ያለ ተጓዥ ከሆነ ፣ አመልካቹ የሽግግር (C1) ቪዛ በተጨማሪ ያስፈልገዋል እናም ከቀጣሪው ወይም ከቀጣሪ ወኪል ይህ ሽግግር እንደሚያሰፈልግ የማረጋገጫ ደብዳቤ ያስፈልጋል። የቆንሱላር ክፍሉ በተለይ C1/D ቅልቅል ቪዛ ይሰጣል የአመልካቹ ሀገር ዜግነት የጋራ ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ የሚፈቅድ ከሆነ። ለበለጠ መረጃ የበለጠ መረጃ የሀገር የጋራ ስምምነት የጊዜ ሰሌዳን በ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/Visa-Reciprocity-and-Civil-Documents-by-Country.html ይመልከቱ።

ማሳሰቢያ፡ የአየር መንገድ የበረራ ሰራተኞች ወይም የባሕር ላይ የመረከብ ሰራተኞች ለቢ1 /ቢ2 እንዲሁም ለ ሲ1 /ዲ ቪዛ በጥምር ሲያመለክቱ የዲኤስ 160 ፎረም ከሞሉ በኃላ፤ የአንድ የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ብቻ በመክፈል ለ ሲ1/ዲ ቪዛ ቀጠሮ ይያዙ፡፡

(I) ሚዲያ እና ጋዜጠኞች

ለሚዲያ (I) ቪዛ ብቁ ለመሆን አመልካቾች ለሚዲያ ቪዛ ብቁ መሆነቻውን በአግባቡ ማሳየት ይኖረብቸዋል። የሚዲያ ቪዛ "የውጭ ሀገር ሚዲያ ተወካዮች" ፣ ዘጋቢዎች ፣ ሬዲዮ ፣ ፊልም ፣ የህትመት እንዱስትሪዎችን ፣ እንቅስቃሴያቸው ለውጭ ሚዲያ ስራ አስፈላጊ የሆነ፣ እንደ ሪፖርተሮች ፣ የፊልም ቡድን ፣ አርታዒ እና በተመሳሳይ ስራ ያሉ፣ ወደ አሜሪካ በሙያቸው ለመሳተፍ የሚጓዙ አባላትን ይጨምራል። አመልካቾቹ በውጭ ሀገር ቢሮ ያለውን የሚዲያ ደርጅቱ ሙያዊ ብቃት ያለው እንቅስቀሴ መሳተፍ አለባቸው። የሚዲያ ቪዛ ብቁ ለመሆን ፣ እንቅስቃሴው መረጃን በማቅረብ አስፈጊ መሆን አለበት እና ባጠቃላይ ዜና ማሰባሰብ ሂደት ፣ ወይም ወቅታዊ የተከሰቱ ክስተቶችን መዘገብ። የስፖርት ዝግጅቶችን መዘገብ በአብዘኛው ለሚዲያ ቪዛ አግባብነት አለው። ሌላ ምሳሌ የሚጨመር ፣ ነገር ግን የማይወሰን ፣ የሚከተሉት ሚዲያ ተያያዥ የሆኑ እንቅስቃሴዎች፡-

 • ዋና ተቀጣሪዎች የወጭ መረጃ ሚዲያ የዜና ዝግጅቶችን ወይም ጥናታዊ ዝግጅቶቸን ምስል በመቅረጽ የተሳተፉ።
 • የሚዲያ አባለት በፊልም መስራትና ስርጭት የሚሰተፉ ሆነው ፊልም የሚሰራለት ነገር መረጃን ሆነ ዜናን ለማሰራጨት የሚያገለግል ከሆነ በቻ ለሚዲያ ቪዛ ብቁ ይሆናሉ። በተጨማሪም፣ ዋናው ምንጭ እና የገንዘብ ስርጭቱ ከአሜሪካ ውጭ መሆን አለበት።
 • በኮንተራት የሚሰሩ ጋዜጠኞች፡ በጋዜጠኞች ባለሙያዎች ድርጅት የተሰጠ ማስረጃዎችን የያዙ ሰዎች፣ በውጭ ሊጠቀሙበት በመረጃ ወይም የባህል ግንኙነት ወይም ዜና በዋናነት ለንግድ መዝናኛነት ወይም ማስታወቂያ ያልተሰበ ምርት በኮንትራት እየሰሩ ከሆነ ።
 • የብቸኛ አምራች ኩባንያዎች ተቀጣሪዎች በጋዜጠኞች ባለሙያዎች ድርጅት የተሰጠ ማስረጃዎችን የያዙ ተቀጣሪዎች ሲሆኑ።
 • የውጭ ጋዜጠኞች በሌላ ሀገር ቅርንጫፍ ቢሮ ወይም የአሜሪካ አውታረመረብ ተቀጽላ ፣ የጋዜጣ ወይም የሌሎች ሚዲያ ማስተላለፊያዎች ጋዜጠኛው ወደ አሜሪካ ሂዶ ለወጭ ሀገር ተመልካቾች ብቻ የአሜሪካ ክስተቶችን ዘገባ የሚያቀርብ ከሆነ።
 • እውቅና የተሰጣቸው ተወካዮች የጉብኝት ቢሮዎች፣ ቁጥጥር ፣ የሚሰሩት ፣ ወይም ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በውጭ መንግስት የሚደገፉ ፣ ስለ ዛች ሀገር በዋናነት እወነተኛ የጎብኝዎች መረጃዎችን በማሰረጨት የተሳተፉ።.

(E1/E2) የጋራ ስምምነት ነጋዴ / የጋራ ስምምነት ባለሀብት

የጋራ ስምምነት ነጋዴ (E1) ወይም የጋራ ስምምነት ባለሀብት (E2) ቪዛ ለአንድ ሀገር ዜጋ ሆኖ ከአሜሪካ ጋር የንግድ እና መተላለፊያ ስምምነት ያላት ሆኖ ወደ አሜሪካ የሚመጣው ትርጉም ያለው ንግድ ለማካሄድ፣ የአገልግሎት ንግድና ቴክኖሎጅን ጨምሮ፣ በዋናነት በአሜሪካና የጋራ ስምምነት ባላት ሀገር ፣ ወይም የድርጅትን ስራ ለማሳደግ የሀገር ዜጋው መውዐለ ነዋዩን ያፈሰሰበትን፣ ወይም ትርጉም ያለው ገንዘብ በማፍሰስ ሂደት ላይ ከሆነ። ለተሳተፊ ሀገርች ዝርዝር ይህን ይመልከቱ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/visa-information-resources/fees/treaty.html.

E1 ስደተኛ ላልሆኑ ፈርጆች የጋራ ስምምነቱ ሀገር ዜጎች ወደ አሜሪካ ሀገር እንደገቡና በአለምአቀፍ ንግድ በቻ በራሳቸው እንዲሳተፉ ይፈቅድላቸዋል።

E2 ስደተኛ ላልሆኑ ፈርጆች የጋራ ስምምነቱ ሀገር ዜጎች ትርጉም ያለው ገንዘብ በአሜሪካ ንግድ ስራ ላይ በማፍሰስ ሂደት ላይ ከሆነወደ አሜሪካ ሀገር እንደገቡ ይፈቅደላቸዋል።

ለበለጠ መረጃ፣ እባከዎን https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/employment/treaty-trader-investor-visa-e.html ይመልከቱ።

(E3) የአውስትራሊያ የተለዩ ባለሙያዎች

የዚህ ቪዛ ፈርጆች በልዩ ሙያ ስራዎች ላይ በጊዜያዊነት ወደ አሜሪካ የሚጓዙ የአውስትራሊያ ዜጎቸ የሚሆን ነው። E3 በተለይ ለአውስትራሊያ ዜጎች ነው፣ የበለጠ ዝርዝረ መረጃ በ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/visa-information-resources/all-visa-categories.html ያገኛሉ።

(H, L, O, P, Q, R)ጊዜያዊ ሰራተኛ/ቅጥር ወይም ሰልጣኛ

አመልከቻ አሜሪካን ሀገር በጊዜያዊነት ስደተኛ ባልሆነ መስራት ከፈለገ ፣ የአሜሪካ የስደተኞች ህግ ፣ አመልካቹ የተለየ ቪዛ ያስፈልገዋል፣ አመልካቹ እንደሚሰራው ስራ አይነት በመመሰረት። አብዘኞቹ ጊዜያዊ ሰራተኞ ፈርጆች የአመልከቹ ቀጣሪ የሚሆነው ወይም ወኪሉ የI-129 ጥያቄ አሰገብቶ በ አሜሪካ የዜግነት እና ስደተኞች አገልግሎት (USCIS) መፈቀድ አለበት አመልከቹ ቪዛ ማመልከት ከመቻሉ በፊት ፣ ለበለጠ መረጃ፣ እባከዎን http://www.uscis.gov/portal/site/uscis ይመልከቱ።.

ግለሰቦች ለጊዜያዊ ሰራተኛ ቪዛ ማመልከት የሚችሉት የአሜሪካ ቀጣሪው I-129 ጥያቄ አስገብቶ በUSCIS ከጸደቀለት በኋላ ነው።የማረጋገጫ ደረሰኝ ቁጥር የሚያሳይ ቀጥሎ USCIS ቅጽ I-797 ይሰጣል። ያ ደረሰኝ ቁጥር በዚህ ግልጋሎት የቀጠሮ ጊዜ ሰሌዳን ለማስያዝ ያስፈልጋል። I-797 እና/ወይም I-129 የወረቀት ቅጅዎች አያስፈልጉም።

(H1-B) ሰዎች በተለየ ሙያ ስራዎች – ለዚህ ቪዛ አመልካቾች ስለ ሰውነት የሀሳባዊ እና ተግባራዊ አጠቃቀም ከፍተኛ ልዩ እውቀትን የሚፈልጉና የከፍተኛ ትምህርት የተለዪ የትምህርት አይነቶችን ማጠናቀቅን ያስፈልጋል። እነዚህ ፈረጆች የፋሽን ሞዴሎቸን እነ መንግስት-ለ-መንግስት ጥናትና እድገት፣ ወይም በመከላከያ ክፍል የሚተዳደሩ የጋራ-ምርት የስራ እቅዶችን ያካትታሉ።

(H-1B1)ነፃ ንግድ ስምምነት ((H-1B1) Free Trade Agreement) - ይህ ቪዛ አይነት የተፈጠረው፣ በአሜሪካ እና ቺሊ እንዲሁም በ አሜሪካና ሲንጋፖር ማካከል በተፈረመው ነፃ ንግድ ስምምነት አማካኝነት ነው፡፡ H-1B1ግዚያዊ ሰራተኞች፣ በተወሰነ የስራ ዘርፍ በግዚያዊነት የሚሰሩን ሰራተኞች ይመለከታል፡፡

ለ H-1B1ቪዛ የሚያመለክቱ ቪዛ አመልካቾች፣ ከአሜሪካን አገር ቀጣሪ የስራ ቅጥር ማስረጃ እንዲሁም ከአሜሪካን አገር በሰራተኞች ጉዳይ ፅህፈት ቤት የተረጋገጠ ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ነዋሪ ያልሆኑ የስራ መጠየቂያ አያስፈልግም፡፡ ስለH-1B1ቪዛ ተጨማሪ መረጃ ለማግነት ይህንን ድህረገፅ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/employment.html ይጎብኙ ፡፡.

(H2-A) ወቅታዊ የእርሻ ሰራተኞች – H2-A ቪዛ የአሜሪካ ሰራተኞች የማይገኙባቸውን ጊዜያዊ የእርሻ ስራዎችን ለመሙላት የአሜሪካ ቀጣሪዎች የውጭ ዜጎቸን ወደ አሜሪካ እን ዲያመጡ ይፈቅዳል።

(H2-B) ጊዜያዊ ወይም ወቅታዊ ከእርሻ ስራ ውጭ ሰራተኞች – H2-B ከእርሻ ውጭ ጊዜያዊ ሰራተኛ መርሀግብር የአሜሪካ ቀጣሪዎች ጊዜያዊ ከእርሻ ስራ ውጭ ስራዎችን ለመሙላትየውጭ ዜጎቸን ወደ አሜሪካ እን ዲያመጡ ይፈቅዳል።

(H3) ስልጣኞች(ከህክምና እና ከመደበኛ ትምህርት ሌላ) – ይህ ቪዘ አይነት የውጭ ዜጎች ወደ አሜሪካ መጥተው በተለያዩ ብዙ ዘርፎች እርሻ ፣ ንግድ ፣ ግንኙነቶች ፣ ፋይናንስ ፣ መንግስት፣ ማጓጓዝ ፣ ሙያተኛ ፣ በተጨማሪም የኢንደስትሪ ዘርፎችስልጠና እንዲያገኙ ይፈቅዳል።

(L) በኩባንያ ተላላፊዎች – ይህ ቪዛ ለአመልካቾች ፣ በተከታታይ ሶስት አመታት፣ በውጭ ለተከታታይ አንድ አመት የተቀጡሩ፣ እና በቅርንጫፍ ፣ በዋናው፣ በሸሪክ፣ ወይም በተቀጽላው አንድ አይነት ቀጣሪ በስራአስኪያጅነት፣ ስራአስፈጻሚነት፣ ወይም በልዩ አውቀት ችሎታ። L ቪዛ የአሜሪካ ቀጣሪዎች ስራአስፈጻሚዎችን ሆነ ስራአስኪያጆችን ከሸሪክ ውጭ ሀገር ቢሮ ወደ አንዱ የአሜሪካን ሀገር ቢሮ እንዲያዘዋውሩ ያስችላቸዋል። ይህ ቪዛ በአሜሪካ የሸሪክ ቢሮ የሌላቸውን የውጭ ኩባንያ ስራአስፈጻሚዎችን ሆነ ስራአስኪያጆችን ድርጅት ለመመስረት አላማ ወደ አሜሪካ እንዲልኩ ያስችላቸዋል።

በአሜሪካ ቢሮ ያለን በብዙ ሀገራት የሚንቀሳቀስ ኮርፖሪሽን ግለሰብ ተቀጣሪዎችን ማስመዝገብ ይችላል ወይም አንድ ፈቃድ ሊያገኝ ይችላል፣ ብላንኬት L መጠይቅ ይባላል፣ በዚሁ ስር ብዙ ስራአስኪያጆችና ስራአስፈጻሚዎች ወደ አሜሪካ ሊገቡበት ይችላሉ። ብላንኬት L መጠይቅ ብቁነት ፣ የበለጠ መረጃ እባከዎትን http://www.uscis.gov/portal/site/uscis ይመልከቱ።

አንዴ ጠያቂው ብላንኬት L ፈቃድን ካገኘ ፣ በL ደረጃ ወደ አሜሪካ ለመግባት የሚፈልጉ የግለሰብ ማመልከቻዎች በእያንዳንዱ አመልካች በመወከል መሞላት አለበት።

(O) የተለየ ችሎታ ያለቸው ሰዎች – የ O ቪዛ የሚሰጠው በሳይንስ፣ አርት፣ ትምህርት፣ ንግድ ወይንም ስፖርት የተለየ ችሎታ ላላቸው፤ ወይንም በፊልም ስራ ወይንም በቴሌቪዥን ኢንዱስትሪ በሀገር ውስጥ ወይንም አለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው ስራ ለሰሩ ነው፡፡ ይህም ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ለተሰማሩ ግለሰቦች ወሳኝ የሆነ አገልግሎት እና እርዳታ የሚሰጡ ግለሰቦችንም ይመለከታል፡፡

(P) አለም አቀፍ እውቅና ያላቸው አትሌቶች፣ አርቲስቶች እና የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች – የP ቪዛን ለማግኘት አመልካቹ ወደ አሜሪካን ሀገር የሚመጣው በግል ወይንም በቡድን ለሚከተሉት ጉዳዮች ነው ተብሎ ይጠበቃል፡

 • በተወሰነ የስፖርት ወይንም የኪነ ጥበብ መድረክ በግል ወይንም በቡድን ለመካፈል ወይንም ለማቅረብ፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ቀጣይ ውጤት ይጠበቃል፡፡
 • በአሜሪካና ሀገር ከሚገኝ ድርጅት ጋር እና በሌላ ሀገር ባለ ድርጅት መካከል በሚደረግ የልውውጥ ፕሮግራም ለመካፈል
 • የተለየ ባሕላዊ የብሄር፣ የትውፊት፣ የባህል፣ የሙዚቃ የትያትር ወይንም የአርት ትዕይንት ለማሳየት፣ ለመቅረፅ፣ ለመተርጎም፣ ለመወከል፣ ለማሰልጠን ወይንም ለማስተማር፡፡

ይህም ከላይ በተጠቀሱት ዘርፎች ለተሰማሩ ግለሰቦች ወሳኝ የሆነ አገልግሎት እና እርዳታ የሚሰጡ ግለሰቦችንም ይመለከታል፡፡

(Q) አለም አቀፍ የባህል ልውውጥ ጎብኝ – ይህ ቪዛ አላማው ተግባራዊ ልምምዶቸን፣ ቅጥሮቸን እና የአመልካቹን መኖሪያ ሀገር ታሪክን ባህልንና ልምድ ልውውጥን ለማቅረብ ነው። Q ስደተኛ ላልሆኑ ቪዛ ለአለም አቀፍ ባህል ልውውጥ መርሀግብሮች በአሜሪካ ዜጎች እና ስደተኞች አገልግሎት (USCIS) የተመረጠ ነው።

(R) ሀይማኖታዊ ሰራተኛ – የሀይማኖት ሰራተኛ (R) ቪዛ አሜሪካ ገብተው በሀይማኖት ስራ ችሎታ በጊዜያዊነት ለመስራት ለሚፈልጉ አመልካቾች ነው።

የሀይማኖት ሰራተኞች የሚያካተው በታወቀ የቀጣሪ አካል የተፈቀደላቸው ሰዎች፣ ሀይማኖታዊ አምልኮዎችን እንዲያካሂዱና በዛ እምነት በተፈቀደላቸው የክህነት አባላት በአብዘኛው ጊዜ፣ የሚፈጸሙትን ሌሎች ተግባርት እና በሀየማኖት ሙያ ወይም ስራ የሚሳተፉ ሰራተኞች ነው፡

 • አመልካቹ የሀይማኖት ከፍል አባል እና እውነተኛ ለትርፍ ያልቆመ ሀይማኖታዊ ደርጅት በአሜሪካ ውሰጥ ያለው መሆን አለበት
 • የሀይማኖት ቡድኑና ሸሪኮቹ ፣ የሚቻል ሲሆን፣ ከግብር ነጻ ይሆናሉ ወይም ከግብር-ነጻ ለመሆን ብቁ ናቸው
 • አመልካቹ የሀይማኖቱ ክፍሉ የሀይማኖት ሰራተኛ ደረጃ ከማመልከቱ በፊት ለሁለት አመታት አባል ነበር ። አመልካቹ የዛ ሀይማኖት ከፍል ሚንስትር ሆኖ ለመስራት አቅዷል፣ ወይም በሀይማኖት ስራ ወይም ሙያ እውነተኛ ለትርፍ ያልቆመ ሀይማኖታዊ ደርጅት (ወይም የግብር-ነጻ የዚህ ደርጅት ሸሪክ)

(TD/TN) NAFTA ባለሙያዎች

የሰሜን አሜሪካ የነጻ ንግድ ስምምነት (NAFTA) የተለየ የምጣኔ ሀብትና የንግድ ልውውጥ ግንኙነቶችን ለአሜሪካ ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ይፈጥራል። ስደተኛ ያልሆነ NAFTA ባለሙያዎች (TN) ቪዛ በአሜሪካ ወይም የውጭ ቀጣሪ አስቀድሞ በተዘጋጀ የንግድ እንቅስቃሴ የካናዳና የሜክሲኮ ዜጋዎች ፣ እንደNAFTA ባለሙያዎች አሜሪካ እንዲሰሩ ይፈቅዳል። ቋሚ መኖሪያ ያለቸው ግለሰቦች – ግን ዜጋ ያለሆኑ –የካናዳ እና የሜክሲኮ እንደ NAFTA ባለ ሙያ ለመስራት ብቁ አይደሉም። የTN ቪዛ ያዝ ጥገኞች የTD ቪዛ ይሰጣቸዋል።.

የካናዳ እና የሜክሲኮ ባለሙያዎች በሚከተሉት ሁኔታዎች ስር አሜሪካ ውስጥ መስራት ይችላሉ፡-

 • አመልካቹ የካናዳ ወይም የሜክሲኮ ዜጋ ነው
 • ሙያው በNAFTA ዝርዝር ላይ አለ
 • በአሜሪካ ያለ የስራ ቦታ የNAFTA ሙያ ያስፈልጋል።
 • የሜክሲኮ ወይም የካነዳ አመልካቾች አስቀድሞ በተዘጋጀ የሙሉ ጊዜ ወይም የትር ጊዜ ስራ ይሰራሉ።
 • የካናዳ ወይም የሜክሲኮ አመልካቾች የሙያው ብቃት አላቸው።

ሌሎች ስደተኛ ያልሆኑ የቪዛ ፈርጆች

(T) ጉዳተኞችን ማዘዋወር

የT ቪዛ ያዥዎች አሰቃቂ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች ናቸው። የሰዎች ዝውውር በተጨማሪ ማዘዋወር ሰዎችን ፣ ዘመናዊ-ቀን ባርነት ቅርጽ ያለወ ሆኖ አዘዋዋሪዎቹ ግለሰቦችን ቅጥርን እና የተሻለ ሕይወት በማልት በውሸት ቃል በመግባት ግለሰቦችን ያስኮበልላሉ። አዘዋዋሪወቹ በአብዛኛው ደሀውን፣ እና ያልተቀጠሩ ግለሰቦች ማህበራዊ አገልግሎቶቸን የማያገኙትን ይጠቀሙባቸዋል። T ስደተኛ ያልሆኑ ደረጃ (T ቪዛ) ተጎጅዎችን ከሰው አዘዋዋሪዎች ይጠብቃቸዋል እንዲሁም ተጎጅዎቹ አሜሪካ በመቆየት በሰው ማዘዋወር ምርመራዎችና ፍርዶችን ያግዛሉ።

የዝውውሩ ተጎጅዎች በአሜሪካ ብቻ T ደረጃ ይሰጣቸዋል። ለበለጠ መረጃ ፣ እባክዎን http://www.uscis.gov/portal/site/uscis ይመልከቱ። የአሜሪካ ኢምባሲና ቆንሱሌት ሚና ለቤተሰብ አባል በአሜሪካ T ደረጃ የሰጣቸውን ብቻ ማመልከቻ ሂደት ይከታተላል።

(U) የወንጀል እንቅስቃሴ ጉዳተኞች

U ቪዛ ፈርጆች የሚገኘው በተለዩ የወንጀል ድርጊቶች ለሚበቁ የውጭ ተጎጅዎች ሆነው በብቁ የወንጀል እንቅስቃሴዎች ምርመራውና በፍርድ የሚያግዙ ናቸው።የ USCIS በቀጥታ የግለሰቦች የራሳቸው-ጥያቄ ፣ U ስደተኛ ያልሆነ ደረጃ በተፈቀደ ጥያቄ በ USCIS ይሰጣል። ሁለቱም U ቪዛ ዋናውና ተከታዩ ጠያቂ ፣ U ደረጃ ፣ በውጭ ሀገራት በሉር ቆንሱላር ክፍሎች ሊያመለክት ይችላል።የ U ቪዛ አላማ የተወሰኑ ወንጀሎች ተጎጅዎቸን ጊዜያዊ የህግ ደረጃ እና አሜሪካ ውስጥ እሰከ 4 አመት እንዲሰሩ የስራ ህጋዊነት ይሰጣል።