የቡድን ቪዛ ጥያቄ ኩባንያዎች፣ የጉዞ ወኪሎች እና ሌሎች ድርጅቶች

አጠቃላይ መልክ

በኢትዮጵያ ለሚያመለክቱ በአንድ ቡድን ለተካተቱ አመልካቾች ቀጠሮ ለማስያዝ ሊከተሏቸው የሚገቡ የተለዩ ሂደቶች ወይም እርምጃዎች የሉም። በአንድ ቡድን 10 ወይንም ከዛ በታች ሆነው ወደ አሜሪካ የሚጓዙ አመልካቾች መለያ በመፍጠር በተለመደው የስደተኛ ላልሆነ ቪዛ ሂደት ማመልከት ይችላሉ፡፡ በአንድ ላይ ቀጠሮ ማስያዝ የሚቻለው ለ10 አመልካቾች ብቻ ነው። በቡድኑ የሚገኙት የአመልካቾች ቁጥር ከ10 ከበለጠ፣ 10 ወይንም ከዛ በታች ቁጥር ያላቸው አመልካቾችን ያካተቱ ብዙ ቡድኖችን በአንድ መለያ/አካውንት ስር መፍጠር ይችላሉ። ነገር ግን፣ በጊዜው እንደሚገኙት የቀጠሮ ቀናት በመወሰን፣ ከአንድ በላይ ቡድኖች ወስጥ የተካተቱ አመልካቾች በሙሉ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ቀጠሮ እንደሚያገኙ ማረጋገጫ የለም።

በአንድ ቡድን ለተካተቱ አመልካቾች ቀጠሮ ለማግኘት ከተቸገሩ በቡድኑ ያሉትን አምልካቾች በመቀነስ ደግመው ይሞክሩ።