አስፈላጊ ሰነዶች

መግለጫ

አመልካቾች ለቆንስላ ክፍሉ ቃለመጠይቅ ሲዘጋጁ ከሚጓዙበት አላማ ጋር ተያያዥነት ያለቸውን አስፈላጊ ሰነዶችን ማሰባሰብ አለባቸው። ከዚህ በታች ለሁሉም የቪዛ ዘርፎች እንዲካተቱ የሚመከሩ ሰነዶች ዝርዝር ይገኛል። በሚያመለክቱት የቪዛ አይነት በዩ.ኤስ. አሜሪካ ህግ መሰረት የተቀመጡትን መስፈርቶች እንደሚያሟሉ ማረጋገጥ ይኖርቦታል፡፡ ቪዛ እንደሚሰጥ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ቪዛ እስከሚሰጥም የመጨረሻ የጉዞ እቅዶችን አይያዙ ወይንም ትኬቶችን አይግዙ፡፡

ያስተውሉ፥ ተጨማሪ ሰነዶች ሊያስፈልጉ ይችላሉ። እባክዎን በሚያመለከቱበት ኤምባሲ ወይም በቆንስላው ድህረገጽ የሚገኘውን እንዴት ቪዛ ማመልከት እንደሚቻል የሚገልጸውን መመሪያ ይመልከቱ። የቪዛ መስፈርቶችን ማሟላቶን ለማረጋገጥ ተጨማሪ ሰነዶችን ሊጠየቁ ይችላሉ።

  1. በቆንስላ ክፍሉ በአካል በመገኘት ቃለመጠይቅ ማድረግ ለሚያሰፈልጋቸው የቪዛ ማመልከቻዎች አመልከቾች የሚያስፈልጉ ሰነዶቻቸውን ሁሉ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  2. በቆንስላ ክፍሉ በአካል በመገኘት ቃለመጠይቅ ማድረግ የማያሰፈልጋቸው የቪዛ አመልከቾች ፣ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን በሙሉ ለቆንስላ ክፍሉ ግምገማ ከማመለከቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አጠቃለይ አስፈላጊ ሰነዶች – ለሁሉም የቪዛ አይነቶች

የሚከተሉት ሰነዶች ሉሁሉም የቪዛ አይነቶች አስፈላጊ ናቸው፡-

  1. ወደ አሜሪካ ለመሄድ የሚያስችል ያልተቃጠለ ፓሰፖርት። ፓስፖርቱ አሜሪካ ከሚቆዩበት ጊዜ ውጭ ቢያንስ ለስድስት ወራት የሚያገለግል መሆን አለበት (በሀገሮች መካከል ባሉ ልዩ ስምምነቶች በስተቀር)
  2. በመጨረሻ የተሰጠውን የአሜሪካ ቪዛ የያዘ ፓስፖርት (የሚመለከትዎ ከሆነ)
  3. ስደተኛ ያልሆነ የቪዛ ማመልከቻዎች ፣ ቅጽ DS-160 ማረጋገጫ ገጽ።
  4. ከዚህ ድህረ ገጽ የታተመ የማረጋገጫ እና መመሪያዎች ገጽ
  5. አንድ 5 x 5 ሴ.ሜ (ወይም 2 x 2 ኢንች) የሆነ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የተነሱት ባለቀለም ፎቶ። ስለ አሜሪካ መንግስት የፎቶ መመሪያዎች ተጨማሪ ዝርዝር በ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/visa-information-resources/photos.html ያገኛሉ።
  6. አብረው ተከትለው የሚጓዙ የቤተሰብ አባሎች ፣ ወደ አሜሪካን አገር በሌላ ምክንያት የሚጓዙ ካልሆነ በስተቀር ለባል ወይም ለሚስት የጋብቻ ሰርቲፊኬት ከ21 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች የልደት ስቲፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ለቃለመጠይቅ በአካል የሚቀርቡ ከሆነ፣ ኦሪጂናል ሰነዶችን ይዘው መቅረብ ይኖርቦታል፡፡ ለእያንዳንዱ የቪዛ አይነት መያያዝ ስላለባቸው ሰነዶች ከዚህ በታች ያለውን ዝርዝር ይመልከቱ፡፡

ተጨማሪ አስፈላጊ ሰነዶች – እንደ ቪዛው አይነት

(B) ጎብኚ: ንግድ ስራ, ቱሪዝም, ለህክምና

  • ለህክምና ከሆነ የሚጓዙት የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ዝግጁ ይሁኑ፡
    • ሀገር ውስጥ ባለ ሀኪም የህክምና ምርመራ ውጤት፣ የበሽታውን አይነት እና አሜሪካን ሀገር ሄዶ መታከም ያስፈለገበትን ምክንያት የሚያስረዳ
    • አሜሪካን ሀገር ከሚገኝ ሀኪም ወይም የህክምና አገልግሎት ሰጭ በሽታውን ለማከም ፈቀደኝነታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ፣ የህክምናውን ወጪና የሚወስደው ጊዜ በዝርዝር(የሀኪሞች ክፍያ፣ ሆስፒታል ተኝቶ ለመታከም የሚጠየቅ ክፍያ፣ እና ሌሎችም ከህክምናው ጋር የተያያዙ ወጪዎች)
    • የበሽተኛው የመጓጓዣ ፣ የህክምና፣ የመኖሪያ ወጪዎች በአሜሪካን ሀገር እንደሚከፈሉ ማረጋገጫ። ይህ በባንክ ወይም ሌሎች ስቴትመንቶች የገቢ፨የቁጠባ ወይም የገቢ ግብር ምላሽ (income tax returns) ማረጋገጫ ሰነዶች(የታካሚው ወይም የህክምናው ወጪ የሚሸፍነው ግለሰብ ወይም ደርጅት)።
  • በአሜሪካ በግል ወይም የሀገር ውስጥ ሰራተኛ ሆነው በተገደበ ሁኔታዎች በጊዜያዊነት ለምስራት ለ B-1ጎብኝ ቪዛ ማመልከት ይችሉ ይሆናል፡፡ እርስዎና አሰሪዎ የስራ ግንኝነት የአሜሪካ የክፍያና የስራ ሁኔታዎችን ማረጋገጥ ይኖርባቸኃል፡፡ እንዴት ማመልከት እንዳለብዎት ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት በአከባቢዎ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤንባሲ ድረ ገጽ እና https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/tourism-visit/visitor.html ይመልከቱ፡፡

በአካል የቆንሱላር ቃለ መጠይቅ በሚቀርቡበት ጊዜ ለቪዛ ብቁ መሆንዎን ለማሳየት ተጫማሪ ሰነዶች ሊጠየቁ ይችላሉ። በአካል የቆንሱላር ቃለ መጠይቅ ላለመቅረብ ብቁ ከሆኑ በተለይ በመመሪያ ገጽ ላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ ሰነዶችን ብቻ ያስገቡ።

ለምሳሌ፤ ለአንድ በአካል ቃለ መጠይቅ በተጨማሪ የሚጠየቁ ሰነዶች ሊያካትቱ የሚችሉት ማስረጃዎች:

  • የጉዞው አላማ
  • ከጉዞዎ በኋላ ከአሜሪካ ለመውጣት ያለዎት ሃሳብ፤ እና/ወይም
  • ሁሉንም የጉዞዎን ወጪዎች የመክፈል ችሎታ።
  • የእርስዎን የጉዞ አላማ እና ወደ መኖሪያ ሀገርዎ ለመመለስ ያለዎትን ሀሳብ ለማሳየት የእርስዎ የቅጥር ማስረጃ እና/ወይም የቤተሰብ ትስስር በቂ ሊሆን ይችላል።
  • ሁሉንም የጉዞዎን ወጪዎች መሸፈን የማይችሉ ከሆነ ሌላ ሰው በከፊል ወይም ሁሉንም የጉዞ ወጪዎን እንደሚሸፍን ማስረጃ ሊያሳዩ ይችላሉ።

(C) በአሜሪካ በኩል መሸጋገር (TRANSITING)

  • አሜሪካ ሀገርን ተሻግረው ወደ ሌላ ሀገር ስለመሄድዎ እንዲሁም አሜሪካን ለቀው ለመሄድ እንዳቀዱ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች
  • አሜሪካ እያሉ ሁሉንም ወጭዎች ለመሸፈን በቂ ገንዘብ መኖሩን የሚያይ ማሰረጃ ።
  • የአሜሪካ ቆይታቸውን እንደጨረሱ አመልካቹ ከአሜሪካ ውጭ ባለ ሀገር የሚለሱበት መኖሪያ እንዳላቸው የሚያሳዩ ማስረጃዎች። ይህን ለማሳየት የአመልካቹን አጠቃለይ የቤተሰብ ፣ የሙያ ፣ የንብረት፣ የቅጥር ሁኔታ፤ እንዲሁም አመልካቹ ከአሜሪካ ውጪ ባለ ሌላ ሀገር ያለውን ሌሎች ግንኙነቶችንና ግዴታዎች በማሳየት የአሜሪካ ቆይታውን ጨርሶ ለመመለስ በቂ ምክኒያት እንዳለው የሚያሳይ ማስረጃ

(D) የቡድን አባል

  • ከቀጣሪው ኩባንያ ደብዳቤ፨ኮንትራት የስራ ጊዜውን የሚገልጽ ከተቻለ ደግሞ አመልካቹ ወደ አሜሪካ የሚገባበትን ቦታ

(E) የጋራ ስምምነት ነጋዴ ወይም የጋራ ስምምነት ባለሀብት

  • ስደተኛ ያልሆነ የጋራ ስምምነት ነጋዴ/የጋራ ስምምነት ባለሀብት ማመልከቻ፣ ቅጽ DS-156E።
  • የእርሰዎን ኩባንያ ሀገር ማንነት የሚያሳይ ሰነዶች።
  • ከቀጣሪዎ የስራ ድርሻዎን የሚዘረዝር እና እርስዎ ስራ አስፈጻሚ ወይም ስራ አስኪያጅ መሆንዎን ወይም ለኩባንያው የስራ ሂደት አስፈላጊና ልዪ ክህሎቶች ያለዎት መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ።
  • በአሜሪካን እና በእርስዎ አገር መሀል ጉልህ የሆነ የንግድ ትስስር ሰለመኖሩ ማስረጃ።
  • ለተጨማሪ ሰንድ መስፈርቶች https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/employment/treaty-trader-investor-visa-e.html ይጎብኙ።

(E3) አውስትራሊያዊ በልዩ ስራ

  • ቅጽ ETA 9035, በግልጽ ተብራርቷል እንደ "E3 - አውስትራሊያ - በሂደትላይ." አስተውል: ይህ ቅጽ የተረጋገጠ የሰውሀይል ሁኔታ ማመልከቻ (LCA) የአሜሪካ ቀጣሪዎች ከሰውሀይል ክፍል የሚያገኙት ነው (DOL)።
  • አሜሪካ ውስጥ ባለ ቀጣሪ ስራ ስለማግኘትዎ ደሞዙ ተጠቅሶ የተጻፈ ደብዳቤ፣ አመልካቹ በልዩ ስራ እንደሚሰማራ የሚገልጽ
  • የተረጋገጠ የውጭ ዲግሪ ቅጅ ሆኖ ከሚያስፈልገው የአሜሪካ ዲግሪ ወይም የተረጋገጠ ቅጅ የአሜሪካ ባችለር ዲግሪ ወይም ከፍተኛ ዲግሪ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ፣ በልዩ ስራው እንደሚያስፈልገው።
  • ስራውን ሊሰራ በታቀደበት ክፍለግዛት አስፈላጊ የሆኑ ፈቃዶች ወይም ሌሎች ህጋዊ ሰነዶች የተረጋገጡ ኮፒዎች። የስራ ፈቃዱ ለመግባት የማያስፈልግ ከሆነ ፣ አመልካቹ ከገባ በኋላ በቂ በሚባል ጊዜ ፈቃድ እንደሚያገኝ የሚያሳይ ማሰረጃ ያስፈልገዋል።

(F) የመደበኛ ትምህርት ወይም የቋንቋ ተማሪ

  • I-20 ፎርም፣ ስደተኛ ላልሆኑ ቪዛ ተመራጭነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ( ወይም ) አካዳሚክ ላልሆኑ፣ የቋንቋ ተማሪዎች እና የሙያ ትምህርቶች የተማሪው ተጨባጭ ሁኔታ፡፡ አመልካቹ ከራሱ ትምህርት ቤት የተሰጠውን እና በ SEVIS የመነጨውን ፎርም፣ I-20፣ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ አመልካቹ እንዲሁም የትምህርት ቤቱ ሃላፊ የ I-20 ፎርሙ ላይ መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
  • የተማሪ እና የልልውጥ ቪዛ ኢንፎረሜሽን ሲስተም (SEVIS) I-901 ክፍያ ደረሰኝ፤ ይህንን ክፍያ መክፈል የሚገባው ማን እንደሆነ የበለጠ መረጃ ለማግኘት SEVP የሚለውን በሚከተለው ድህረገፅ ይጎብኙ http://www.fmjfee.com፡፡

በአካል የቆንሱላር ቃለ መጠይቅ በሚቀርቡበት ጊዜ ለቪዛ ብቁ መሆንዎን ለማሳየት ተጫማሪ ሰነዶች ሊጠየቁ ይችላሉ። በአካል የቆንሱላር ቃለ መጠይቅ ላለመቅረብ ብቁ ከሆኑ በተለይ በመመሪያ ገጽ ላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ ሰነዶችን ብቻ ያስገቡ።

ለምሳሌ፤ ለአንድ በአካል ቃለ መጠይቅ በተጨማሪ የሚጠየቁ ሰነዶች ሊያካትቱ የሚችሉት ማስረጃዎች:

  • የጉዞው አላማ
  • ከጉዞዎ በኋላ ከአሜሪካ ለመውጣት ያለዎት ሃሳብ፤ እና/ወይም
  • ሁሉንም የጉዞዎን ወጪዎች የመክፈል ችሎታ።
  • የእርስዎን የጉዞ አላማ እና ወደ መኖሪያ ሀገርዎ ለመመለስ ያለዎትን ሀሳብ ለማሳየት የእርስዎ የቅጥር ማስረጃ እና/ወይም የቤተሰብ ትስስር በቂ ሊሆን ይችላል።
  • ሁሉንም የጉዞዎን ወጪዎች መሸፈን የማይችሉ ከሆነ ሌላ ሰው በከፊል ወይም ሁሉንም የጉዞ ወጪዎን እንደሚሸፍን ማስረጃ ሊያሳዩ ይችላሉ።

(H) ጊዜያዊ ሰራተኛ

  • ከ I-129ወይም ኖቲስ ኦፍ አክሺንForm I-797ላይ ያለያለ የደረሰኝ ቁጥር፡፡ ይህ ለto H1B1ቪዛ አመልካቾች አይመለከትም፡፡
  • ከአሜሪካን አገር ቀጣሪ የተገኘ የስራ ውል እንዲሁም በአሜሪካ የሰራተኛ ጉዳዮች የተረጋጠ ማመልከቻ የሚያስፈልገው ለ H1B1 ቪዛ አመልካቾች ብቻ ነው፡፡

(I) ሚዲያ እና ጋዜጠኞች

  • የቅጥር ማረጋገጫ
  • ህጋዊ የፕረስ መታወቂያ ኮፒ, የሚመለከትዎት ከሆነ

(J) የልውውጥ ጎበኝ

  • ለልውውጥ የጎብኚ ጉዞ የብቁነት ማረጋገጫ ኦሪጅናል ሰርተፍኬት፣ DS-2019 ቅጽ - በ SEVIS የመነጨ DS-2019 ቅጽ በፕሮግራሙ ስፖንሰር ስፖንሰር አድራጊው የተለዋዋጭ ጎብኝዎችን መረጃ ወደ SEVIS ስርዓት ከገባ በኋላ የሚገኝ ነው። .ሁሉም የልውውጥ ጎብኝዎች ፣ የእነርሱ ባለቤቶች እና ወጣት ልጆች፣ በአሜሪካ ውስጥከተማሪው ጋር ለመኖር ከፈለጉ በተማሪ እና ልውውጥ ጎብኝ መረጃ ስርዓት (SEVIS) መመዝገብ አለባቸው። እያንዳንዱ ግለስብ DS-2019 ቅጽ ይቀበላል።
  • ስልጠና/የልምምድ ስራ አመዳደብ እቅድ, ቅጽ DS-7002 – ከቅጽ DS 2019 በተጨማሪ ፣ በ J-1 ሰልጣኝ እና ተለማማጅ ፈርጆች DS 7002 (መሰረት ያደረገ ሳጥን 7 በ ቅጽ DS-2019)ያሰፈልጋቸዋል። ስለ ሰልጣኝ እና ተለማማጅ መርሀግበሮች የበለጠ ለመረዳት በ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/study.html.
  • የተማሪ እና የልልውጥ ቪዛ ኢንፎረሜሽን ሲስተም (SEVIS) I-901 ክፍያ ደረሰኝ፤ ይህንን ክፍያ መክፈል የሚገባው ማን እንደሆነ የበለጠ መረጃ ለማግኘት SEVP የሚለውን በሚከተለው ድህረገፅ ይጎብኙ http://www.fmjfee.com፡፡

በአካል የቆንሱላር ቃለ መጠይቅ በሚቀርቡበት ጊዜ ለቪዛ ብቁ መሆንዎን ለማሳየት ተጫማሪ ሰነዶች ሊጠየቁ ይችላሉ። በአካል የቆንሱላር ቃለ መጠይቅ ላለመቅረብ ብቁ ከሆኑ በተለይ በመመሪያ ገጽ ላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ ሰነዶችን ብቻ ያስገቡ።

ለምሳሌ፤ ለአንድ በአካል ቃለ መጠይቅ በተጨማሪ የሚጠየቁ ሰነዶች ሊያካትቱ የሚችሉት ማስረጃዎች:

  • የጉዞው አላማ
  • ከጉዞዎ በኋላ ከአሜሪካ ለመውጣት ያለዎት ሃሳብ፤ እና/ወይም
  • ሁሉንም የጉዞዎን ወጪዎች የመክፈል ችሎታ።
  • የእርስዎን የጉዞ አላማ እና ወደ መኖሪያ ሀገርዎ ለመመለስ ያለዎትን ሀሳብ ለማሳየት የእርስዎ የቅጥር ማስረጃ እና/ወይም የቤተሰብ ትስስር በቂ ሊሆን ይችላል።
  • ሁሉንም የጉዞዎን ወጪዎች መሸፈን የማይችሉ ከሆነ ሌላ ሰው በከፊል ወይም ሁሉንም የጉዞ ወጪዎን እንደሚሸፍን ማስረጃ ሊያሳዩ ይችላሉ።

(ኬ)የአሜሪካ ዜጋ እጮኛ ወይም ባለቤት

(L) በኩባንያ ተላላፊዎች

  • ለተፈቀደለወት አቤቱታ የደረሰኝ ቁጥር ስደተኛ ላለሆኑ ሰራተኞች እንደሚታየው፣ ቅጽ I-129 ወይም የድሪጊት ማሳወቂያ፣ ቅጽ I-797 ፣ ከ USCIS።
  • የኤል ቪዛ ቡድን ውስጥ የተካተቱ ከሆኑ ሁለት የI-129S ፒቲሽን ፎርም ኮፒ በቃለመጠይቆ ወቅተ ይዘው መቀረብ ይኖርቦታል፡፡
  • የኤል ‹ብላንኬት› ማመልከቻ (L blanket petition) ዋና አመልካች ማጭበርበሮችን የመከላከያ እና ማግኛ ክፍያ 500 የአሜሪካ ዶላር በቃለመጠይቆ ወቅት መክፈል ይኖርቦታል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/visa-information-resources/fees/fees-visa-services.html ይጎብኙ፡፡
  • በተጨማሪም የ የኤል ‹ብላንኬት› ማመልከቻ (L blanket petition) አንዳንድ አመልካቾች ተጨማሪ ክፍያዎች መክፈል ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ https://www.uscis.gov/forms/h-and-l-filing-fees-form-i-129-petition-nonimmigrant-worker ይጎብኙ፡፡

(M) ሙያ ነክ/መደበኛ ትምህርት ያልሆነ ተማሪ

  • ቅጽ I-20 - አንድ ጊዜ የተማሪውን መረጃ በ SEVIS ውሂብ ቋት እንደገባ ትምህርት ቤቱ SEVIS የተዘጋጀ I-20 ቅጽ ይልካል። ተማሪው እና የትምህርት ቤቱ ባለስልጣን I-20 ቅጽ ላይ መፈረም አለባቸ።ሁሉም ተማረዎች፣ የእነርሱ ባለቤቶች እና ወጣት ልጆች፣ በአሜሪካ ውስጥከተማሪው ጋር ለመኖር ከፈለጉ በተማሪ ልውውጥ ጎብኝ ስርዓት (SEVIS) መመዝገብ አለባቸው። እያንዳንዱ ግለስብ I-20 ቅጽ ይቀበላል።
  • የተማሪ እና የልልውጥ ቪዛ ኢንፎረሜሽን ሲስተም (SEVIS) I-901 ክፍያ ደረሰኝ፤ ይህንን ክፍያ መክፈል የሚገባው ማን እንደሆነ የበለጠ መረጃ ለማግኘት SEVP የሚለውን በሚከተለው ድህረገፅ ይጎብኙ http://www.fmjfee.com፡፡

በአካል የቆንሱላር ቃለ መጠይቅ በሚቀርቡበት ጊዜ ለቪዛ ብቁ መሆንዎን ለማሳየት ተጫማሪ ሰነዶች ሊጠየቁ ይችላሉ። በአካል የቆንሱላር ቃለ መጠይቅ ላለመቅረብ ብቁ ከሆኑ በተለይ በመመሪያ ገጽ ላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ ሰነዶችን ብቻ ያስገቡ።

ለምሳሌ፤ ለአንድ በአካል ቃለ መጠይቅ በተጨማሪ የሚጠየቁ ሰነዶች ሊያካትቱ የሚችሉት ማስረጃዎች:

  • የጉዞው አላማ
  • ከጉዞዎ በኋላ ከአሜሪካ ለመውጣት ያለዎት ሃሳብ፤ እና/ወይም
  • ሁሉንም የጉዞዎን ወጪዎች የመክፈል ችሎታ።
  • የእርስዎን የጉዞ አላማ እና ወደ መኖሪያ ሀገርዎ ለመመለስ ያለዎትን ሀሳብ ለማሳየት የእርስዎ የቅጥር ማስረጃ እና/ወይም የቤተሰብ ትስስር በቂ ሊሆን ይችላል።
  • ሁሉንም የጉዞዎን ወጪዎች መሸፈን የማይችሉ ከሆነ ሌላ ሰው በከፊል ወይም ሁሉንም የጉዞ ወጪዎን እንደሚሸፍን ማስረጃ ሊያሳዩ ይችላሉ።

(O) የወጭ ሀገር የተለየ ችሎታ ያለቸው

  • ለተፈቀደለወት አቤቱታ የደረሰኝ ቁጥር ስደተኛ ላለሆኑ ሰራተኞች እንደሚታየው፣ ቅጽ I-129 ወይም የድሪጊት ማሳወቂያ፣ ቅጽ I-797 ፣ ከ USCIS።

(P) አለም አቀፍ እውቅና ያለቸው የውጭ ሀገር ዜጎች

  • ለተፈቀደለወት አቤቱታ የደረሰኝ ቁጥር ስደተኛ ላለሆኑ ሰራተኞች እንደሚታየው፣ ቅጽ I-129 ወይም የድሪጊት ማሳወቂያ፣ ቅጽ I-797 ፣ ከ USCIS።

(Q) የባህል ልውወጥ ጎብኝ

  • ለተፈቀደለወት አቤቱታ የደረሰኝ ቁጥር ስደተኛ ላለሆኑ ሰራተኞች እንደሚታየው፣ ቅጽ I-129 ወይም የድሪጊት ማሳወቂያ፣ ቅጽ I-797 ፣ ከ USCIS።

በአካል የቆንሱላር ቃለ መጠይቅ በሚቀርቡበት ጊዜ ለቪዛ ብቁ መሆንዎን ለማሳየት ተጫማሪ ሰነዶች ሊጠየቁ ይችላሉ። በአካል የቆንሱላር ቃለ መጠይቅ ላለመቅረብ ብቁ ከሆኑ በተለይ በመመሪያ ገጽ ላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ ሰነዶችን ብቻ ያስገቡ።

ለምሳሌ፤ ለአንድ በአካል ቃለ መጠይቅ በተጨማሪ የሚጠየቁ ሰነዶች ሊያካትቱ የሚችሉት ማስረጃዎች:

  • የጉዞው አላማ
  • ከጉዞዎ በኋላ ከአሜሪካ ለመውጣት ያለዎት ሃሳብ፤ እና/ወይም
  • ሁሉንም የጉዞዎን ወጪዎች የመክፈል ችሎታ።
  • የእርስዎን የጉዞ አላማ እና ወደ መኖሪያ ሀገርዎ ለመመለስ ያለዎትን ሀሳብ ለማሳየት የእርስዎ የቅጥር ማስረጃ እና/ወይም የቤተሰብ ትስስር በቂ ሊሆን ይችላል።
  • ሁሉንም የጉዞዎን ወጪዎች መሸፈን የማይችሉ ከሆነ ሌላ ሰው በከፊል ወይም ሁሉንም የጉዞ ወጪዎን እንደሚሸፍን ማስረጃ ሊያሳዩ ይችላሉ።

(R) ሀይማኖታዊ ሰራተኛ

(T) ተጎጅዎች ዝውውር

  • ቅጽ I-797, መስታወስ ድሪጊት, ቅጽ USCIS ቅጽ I-914 ማጽደቅን የሚያሳይ, አባሪ A

(TD/TN) NAFTA ባለሙያዎች

  • የቅጥር ማረጋገጫ

(U) የወንጀል እንቅስቃሴ ጉዳተኛ

  • ቅጽ I-797, መስታወስ ድሪጊት, ቅጽ USCIS የ U ስደተኛ ያልሁኑ አቤቱታወች ማጽደቅን የሚያሳይ