ለዲፕሎማቶች፣ ለመንግስት ተወካዮች፣ ለኤምባሲ ሠራተኞች፣ ለፉልብራይት ምሁራን/ ስኮላሮች የሚሆኑ ቪዛዎች

ዲፕሎማቶች፣ የመንግስት ተወካዮች፣ የኤምባሲ ሠራተኞች፣ የኔቶ (NATO) ሠራተኞች

የዲፕሎማቲክ (A)፣ የዓለምአቀፍ ድርጅት (G) እና የኔቶ (NATO) ቪዛዎች ወደ አሜሪካ ለሚጓዙ ዲፕሎማቶችና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣኖች የሚሰጡ ቪዛዎች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ አንድ ዲፕሎማት ወይንም ሌላ የመንግስት ባለስልጣን የሚያስፈልጋቸው የቪዛ አይነት ወደ አሜሪካ በሚጓዙበት አላማ ላይ የተወሰነ ነው፡፡ በአሜሪካ የኢሚግሬሽን ህግ መሠረት ለ A፣ G፣ ወይም የኔቶ (NATO) ቪዛ ብቁ ለመሆን አመልካቾች ማሟላት የሚገባቸው በጣም ውስን የሆኑ መስፈርቶች አሉ፡፡

አብዛኞቹ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ያላቸው እና ለባለስልጣን (ኦፊሻል) ቪዛ የሚያመለክቱ ግለሰቦች ከቪዛ (MRV) ክፍያ ነፃ ናቸው፡፡ ለእነዚህ የቪዛ አይነቶች የሚያመለክቱ አመልካቾች ይህንን አገልግሎት መጠቀም የለባቸውም ምክኒያቱም በስህተት የተከፈለም ቢሆን የተከፈለ የቪዛ (MRV) ክፍያ ተመላሽ አይደረግም፡፡

የዲፕሎማቲክ እና የባለስልጣን (ኦፊሻል) ቪዛዎችን የሚመለከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/other-visa-categories/visas-diplomats.html ይጎብኙ፡፡

የኔቶ (NATO) ቪዛዎችን የሚመለከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ይጎብኙ፡ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/other-visa-categories/visa-employees-nato.html፡፡

ዲፕሎማቶች፣ የመንግስት ተወካዮች፣ የኤምባሲ ሠራተኞች፣ የዓለም አቀፍ (IO) እና የኔቶ (NATO) ሠራተኞች ማመልከቻዎቻቸውን በቀጥታ ለኤምባሲው/ ለቆንስላው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ሰለዚህ ሂደት አጀማመር የተወሰነ መረጃ ለማግኘት ተጓዡ አዲስ አበባ ወደሚገኘው የዩኤስ ኤምባሲ ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 5 ሰዓት እስከ 6 ሰ ዓት ባለው ግዜ በመሄድ እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ መጠየቅና አመራር መቀበል ይችላሉ።


የፉልብራይት ምሁራን/ስኮላሮች ወይም የሌሎች በአሜሪካ መንግስት ስፖንሰር የሚደረጉ ፕሮግራሞች ተሳታፊዎች

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (Department of State)፣ በአሜሪካ የዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት (USAID) ወይም በአሜሪካ መንግስት የሚደጎም የትምህርት እና የባህላዊ የልውውጥ ፕሮግራም ተሳታፊዎች የሆኑና በ DS-2019 ቅጽ - ማለትም የልውውጥ ጎበኚ (J) ብቁነት ምስክር ወረቀት (Certificate of Eligibility for Exchange Visitor (J) Status) ላይ በG-1፣ G-2፣ G-3፣ ወይም G-7 የሚጀምሩ የፕሮግራሙ ተከታታይ ቁጥሮች የታተሙበት ከሆነ የፉልብራይት ምሁራን/ስኮላሮች ወይም የሌሎች በአሜሪካ መንግስት ስፖንሰር የተደረጉ የልውውጥ ጎብኚ (J) ቪዛ አመልካቾች እና ጥገኞቻቸው የቪዛ ማመልከቻ ክፍያዎችን መክፈል አያስፈልጋቸውም፡፡

አጋዥ አገናኞች፡
የልውውጥ ጎብኚ ፕሮግራም (J) ቪዛ
የትምህርታዊ እና የባህላዊ ጉዳዮች የልውውጥ ፕሮግራሞች ቢሮ

የቪዛ ክፍያ ማስፈለግ አለማስፈለጉን የመወሰን ኃላፊነት የእያንዳንዱ ተጓዥ ነው፡፡

አንድ ተጓዥ ክፍያ ለሚያስፈልገው የቪዛ አይነት ማመልከት ካስፈለጋቸው ለቪዛ ለማመልከት ይህንን አገልግሎት በመጠቀም ቀጠሮ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከስደተኛ ያልሆነ ቪዛ (NIV) ገጽ ላይ "የአሜሪካ ስደተኛ ያልሆነ ቪዛ ማመልከቻ (ዲኤስ-160) ቅጽ ሞልቻለሁ፤ እናም ለቪዛ ማመልከት አለብኝ።" የሚለውን ምርጫ ይምረጡ፡፡

ተጓዡ የቪዛ (MRV) ክፍያ ሳይከፍሉ ለመጓዝ ብቁ ከሆኑ ማመልከት የሚፈልጉበትን የቆንስላ ክፍል በቀጥታ በሚከተለው ማግኘት ይኖርባቸዋል፡

addisniv@state.gov