የቪዛ ሰነዶች ማስገቢያ የፖስታ መልዕክት አገልግሎቶች

መግለጫ

የመልዕክት አገልግሎት ማቅረብ በቪዛ ማመልከቻ ሂደት ደጋፍ ጋር ተጨምሯል። የመልዕክት አገልግሎት ማቅረቡ ሰነዶችን ከአሜሪካ ቆንስላ ክፍል መላክንና መወሰድን ሊያካትት ይችላል።

የመልዕክት አገልግሎት አቅራቢው ከማንኛውም የቪዛ ማማልከቻዎች ጋር ለተያያዙ ጭነቶች የመከታተያ ቁጥር እንደመደበለት ወዲያውኑ አውቶሜትድ ኢሜይል ይላካል። አንዴ የመከታተያ ቁጥር ለጭነቱ እንደተመደበለት ፣ ሰነዱ ያለበትን ሁኔታ በዚህ ድህረገጽ ወይም የመልዕክት አገልግሎት አቅራቢውን ደህረገጽ በመጠቀም መከታተል ይቻላሉ።

ከዚህ በታች ያለውን መረጃ አንብበውም ስለ ሰነድዎ መመለስ ተጨማሪ ጥያቄ ወይንም ችግር ካጋጠምዎ በዚህ ድህረገፅ ያነጋግሩን ገጽ ላይ የሰነድ የማድረስ ጉዳይ ስር የተፃፋን መመሪያ ይከተሉ፡፡


የመልዕክት አገልግሎት አቅራቢ- መመለሻ አገልግሎት

አግባብ ያላቸው የቪዛ ሰነዶች በሙሉ የሚመለሱት በተመረጠው አገልገሎት በኩል ነው (ከአገልገሎት መስጫ ቦታዎች ለመረከብ ወይም የመረከቢያ አድራሻ)።

ያስተውሉ: እያንዳንዱ የአሜሪካ ቪዛ ማመልከቻ የተለየ ነው። የአሜሪካ ቆንስላ ክፍል የውሳኔ ሂደት ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ በዚህ አገልገሎት መረጃ ሊሰጥ አይችልም። የአሜሪካ ቆንስላ ክፍል ሰነዶችን አንዴ ለፖሰታ አገልግሎት ሰጪው ካስተላለፈ በኋላ ሰነዶቹን ለመውሰድ እስከ 3 የስራ ቀናት ይወስዳል።

የመውሰጃ ቦታን በመጠቀም ሰነዶችን የመመለስ አገልግሎት

የቪዛ ሰነዶቻቸው ለመወሰድ ዝግጁ እንደሆኑ አመልካቾች በኢሜይል ይነገራቸዋል፡፡ ከሚከተሉት በአንዱ መንገድ አመልካቾች ማንነታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፡

  1. የግል ሰነዶቻቸውን ለመውሰድ የሚፈልጉ አመልካቾች ማንነታቸውን ለማረጋገጥ ከሚከተሉት ማናቸውንም ሰነዶች ማቅረብ ይችላሉ፡
    • በመንግስት የተሰጠ መታወቂያ (ፎቶ ያለው)
    • የመንጃ ፈቃድ (ፎቶ ያለው)
    • የልደት ሰርተፊኬት
  2. የልጆቻቸውን ሰነዶች ለመውሰድ የሚፈልጉ ወላጆች ልጆቻቸው እንደሆኑ ለማሳየት ከሚከተሉት ማናቸውንም ሰነዶች ማቅረብ ይችላሉ፡
    • የልጁ የልደት ሰርተፊኬት ወይንም የጉድፈቻ ውሳኔ፤ ቢያንስ የአንዱ ወላጅ ሙሉ የህግ ስም ሰነዱ ላይ መጠቀስ አለበት፡፡
    • በተራ ቁጥር 1 ስር ከተዘረዘሩት ሰነዶች መሃከል አንዱን በማቅረብ ወላጅ ማንነቱን ማሳየት እና ስሙም በልጁ የልደት ሰርተፊት ወይንም የጉዲፈቻ ውሳኔ ላይ ከተጠቀሰው ጋር እንደሚመሳሰል ማሳየት ይኖርበታል፡፡
  3. አዋቂ አመልካቾች ሶስተኛ ወገን ፓስፖርታቸውንና ሰነዶቻቸውን እንዲረከብ ፈቃድ መስጠት ይችላሉ፡፡ ሶስተኛው ወገን የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይኖርበታል፡
    • ህጋዊ የውክልና ማስረጃ
    • በተራ ቁጥር 1 ከተዘረዘሩት ሰነዶች መሃከል አንድ የአመልካቹ የመታወቂያ ፎቶ ኮፒ ሶስተኛ ወገኑም በተራ ቁጥር 1 ከተዘረዘሩት መሃከል አንድ መታወቂያ ማሳየት ይኖርበታል፡፡
    • መታወቂያው ላይ ያለው ስም የውክልና ማስረጃ ላይ ከተጠቀሰው ስም ጋር አንድ መሆን አለበት

በሰላሳ (30) ቀን ውስጥ ያልተወሰደ ማንኛውም ሰነድ ለቆንስላ ክፍሉ ተመላሽ ይደረጋል፡፡


የመልዕክት አገልግሎት አቅራቢ- የመላክ አገልግሎት

በቪዛ ማመልከቻ ሂደት አመልከቹ በቆንስላ ክፍሉ በአካል መገኘት ሳያስፈልው ለማመልከቻው ደጋፊ የሆኑ ማስረጃዎችን ለማቅረብ የሚያስችሉት የተለያዩ ሁኔታዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ከነዚህ ሁኔታዎች አንዱ በተከሰተ ጊዜ የሰነድ መላኪያ ፈቃድ ማረጋገጫ እንዴት ማተም እንደሚቻል የሚገልጸውን መመሪያ ቀጠሮ በሚያዝበት ጊዜ በዚህ ድህረገጽ ይገኛል። የሰነድ መላኪያ ፈቃድ ማረጋገጫ አመልካቾች ሰነዶችን በመልዕክት አገልግሎት አቅራቢ በኩል ያለ ምንም ክፍያ ወደ ቆንስላ ክፍሉ እንዲልኩ ያስችላል።

የዲኤችኤል ኢትዮጵያ ቦታዎች