የቪዛ ክፍያዎች

አጠቃለይ የክፍያ መረጃ

ሁሉም የቪዛ አመልካቾች፣ ሕጻናትን ጨምሮ የማይመለስ እና የማይዘዋወር ስደተኛ ላልሆኑ ቪዛ (MRV) የማመልከቻ ክፍያ ይከፍላሉ። እባክዎን ከዚህ በታች ያሉትን አማራጮችና መመሪያዎች ይመልከቱ። የአሜሪካ ቪዛ ቢሰጠዎም ባይሰጠዎም የቪዛ ማመልከቻው ክፍያ መክፈል ያስፈልጋል።


የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ የአከፋፈል ስርዓቶች

  • በጥሬ ገንዘብ ይክፈሉ
    1. እዚህ ድህረገጽ ላይ አዲስ አመልካች ይፍጠሩ።
    2. የአመልካቹን መረጃ በመጨመር የምዝገባውን ሂደት ያጠናቁ።
    3. የክፍያው ገጽ ላይ እስኪደርሱ የድህረግጹን ሂደት ይከተሉ።
    4. በጥሬ ገንዘብ ይክፈሉ የሚለውን ይምረጡ።
    5. በጥሬ ገንዘብ የክፍያ ማዘዣ ገጹን ያውርዱ (ዳውንሎድ ያድርጉ)፣ ያትሙ፤ ማዘዣው ላይ ያለውን ትዕዛዝም ይከተሉ።
    ያስተውሉ፥
    1. አንዴ ክፍያውን ከፈፀሙ ክፍያው ተረጋግጦ ቀጠሮ ለመየዝ እስከ 2 የስራ ቀን ሊወስድ ይችላል፡፡ ክፍያው ሲረጋገጥ ቀጠሮ መያስ ይችላሉ፡፡
    2. የመክፈያው ወረቀተወ ለአንድ ግዜ ክፍያ ብቻ ነው የሚያገለግለው፡፡

የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ ደንብና ሁኔታዎች

የ ዩ ኤስ ቪዛ ማመልከቻ (MRV) ክፍያዎች፡-

  • የማይመለስ — የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ለቪዛ ማመልከቻ ተቀበላቸውን ክፍያዎችን ተመላሽ አያደርግም።
  • የማይተላለፍ — የቪዛ ማመልከቻ ክፍያዎች እንደገና ሊሸጡ ወይም ወደ ሌላ አመልካች ሊዛወሩ አይችሉም።
  • ለአንድ ማመልከቻ ብቻ የሚያገለግሉ — የቪዛ ማመልከቻ ክፍያ የሚያገለግለው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው። የቀረበው የቪዛ ማመልከቻው ተቀባይነት ካላገኘ፣ በድጋሚ ለማመልከት አዲስ የቪዛ ማመልከቻና ክፍያ ማቅረብ ያስፈልጋል።
  • ከ 1 አመት በኋላ አያገለግሉም — የቪዛ ማመልከቻ ክፍያዎች ከተገዙበት ቀን ጀምሮ ለ365 ቀናት ያገለግላሉ። የክፍያው አገልግሎት ጊዜ ያበቃል እናም ክፍያውን ለቪዛ ማመልከቻ የመጠቀም መብተዎን ያጣሉ።
  • በአንድ የተወሰነ ሀገር የተከፈሉ የቪዛ ክፍያዎች ወደሌላ ሀገር ሊተላለፉ አይችሉም። በአንድ የተወሰነ ሀገር ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ ያንን ክፍያ በመጠቀም በሌላ ሀገር የቪዛ ቀጠሮ ማስያዝ አይችሉም። በእዛው ሀገር ቀጠሮዎን መቀየር የሚፈልጉ ከሆነ በዚህ ድህረ ገጽ በመለያዎ በመግባት ቀጠሮዎን ሊሰርዙ ወይንም በድጋሚ ሊያሲዙ ይችላሉ። ይህንንም ለማድረግ ተጨማሪ ክፍያ መክፈል አያኖርቦትም።

ለአሜሪካ ቪዛ (MRV) ክፍያዎች ጊዜ ሰሌዳ

$185 USD

(B) ጎብኝ: ንግድ ስራ, ቱሪዝም, ሕክምና ለማግኘት
(C) በአሜሪካ ውስጥ ተሸጋጋሪ
(D) የቡድን አባል
(F) የመደበኛ ትምህርት ተማሪ
(M) ሙያ ነክ/ከመደበኛ ትምህርት ውጭ ተማሪ
(I) ሚዲያ ወይም ጋዜጠኛ
(J) የልውውጥ ጎበኝ
(TD/TN) NAFTA ባለሙያ
(T) የአዘዋዋሪዎች ተጎጅ
(U) የወንጀል እንቅስቀሴዎች ተጎጅ

$205 USD

(H) ጊዜያዊ ሰራተኛ/ቅጥር ወይም ሰልጣኝ
(O) የተለየ ችሎታ ያለው ሰው
(P) አትሌቶች ፣ ከያነያን፣ አዝናኞች
(Q) አለም አቀፍ የባህል ልውውጥ ጎብኝ
(R) የሀይማኖት ሰራተኛ
(L) በኩባንያ ተላላፊዎች

$315 USD

(E1) የጋራ ስምምነት ነጋዴ
(E2) የጋራ ስምምነት ባለሀብት
(E3) የአውስትራሊያ የተለየ ባለሙያ

$265 USD

(K) የአሜሪካ ዜጋ እጮኛ ወይም ሚስት


ለቪዛ አመልካቾች ተጨማሪ ክፍያዎች

ከቪዛ ማመልከቻ (MRV) ክፍያዎች ውጭ ተጨማሪ ክፍያዎች ያስፈልጋሉ ስደተኛ ያልሆነ ቪዛዎችን ለማግኘት ሲፈለግ። ለእርሰዎ የቪዛ ማመልከቻ የሚውሉ ተጨማሪ ክፍያዎች አይነቶቸ፡-

SEVIS ክፍያ

ተማሪ (F, ወይም M) እና የልውውጥ ጎብኝ (J) ቪዛ አመልካቾች የተለየ SEVIS (ተማሪ እና የልውውጥ ጎበኝ መረጃ ሰርዓት) ክፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል። የተማሪ ወይም የልውውጥ ጎብኝ ቪዛ ከመሰጠቱ በፊት የክፍያ ማረጋገጫ ያስፈልገዋል። ዠርዝር መረጃ ስለ SEVIS እና ሰለ ክፍያ አከፋፈል መመሪያዎቸን በዚህ ያገኛሉ http://www.ice.gov/sevis

የጋራ ስምምነት ጊዜ ሰሌዳ ክፍያ

የአመልካቹ ሀገር ዜግነት እና የቪዛ አይነት ሁኔታ ፣ አመልካቹ ተጨማሪ ክፍያዎችን ቪዛን ለማግኘት እንዲከፍል ሊጠበቅበት የችላል ፣ የጋራ ስምምነት ጊዜ ሰሌዳ ከፍያ ይባለል። ዠርዝር መረጃ ስለ የጋራ ስምምነት ጊዜ ሰሌዳ ከፍያ በዚህ ያገኛሉ https://travel.state.gov/content/travel/en/us-visas/Visa-Reciprocity-and-Civil-Documents-by-Country.html